ኢትዮጵያ የ261 ሚሊዮን ዶላር ብድርን የምታገኘው ከውሳኔ በኋላ መሆኑን አይ.ኤም.ኤፍ. አስታወቀ

Date:

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ.ኤም.ኤፍ) እና የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ ብድር አቅርቦት መርሃ ግብር የአራተኛ ዙር ግምገማን ለመደምደም የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል። ስምምነቱ ጸድቆ ወደሥራ በሚውልበት ወቅት ኢትዮጵያ የ261 ሚሊዮን ዶላር የብድር አቅርቦት የምታገኝ መሆኑም ተገልጿል።

ስምምነቱ የተፈጸመው በአልቫሮ ፒሪስ የተመራው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ቡድን በተቋሙ የገንዘብ መለኪያ መርሃ ግብር የሚደገፈውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና በኢትዮጵያ መንግስት ቅድሚያ ትኩረት የተሰጣቸውን ፖሊሲዎች አፈጻጸም ሁኔታ ከመርሃ ግብሩ አራተኛ ዙር የአፈጻጸም ግምገማ አኳያ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 30 እስከ ሕዳር 23 ቀን 2025 በአዲስ አበባ ሲገመግም ከቆየ በኋላ ነው።

ውይይቱ በበይነ መረብና በአካል ከታሕሳስ 3 እስከ 5 ቀን 2025 ቀጥሎ ከተካሄደ በኋላ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም በአራተኛው ዙር ግምገማው ለኢትዮጵያ የ261 ሚሊዮን ዶላር የብድር አቅርቦት ለመስጠት የወሰነ ሲሆን ይህም እስካሁን ተቋሙ ለኢትዮጵያ የሰጠውን የብድር መጠን 2 ሺሕ 134 ሚሊዮን ዶላር ያደርሰዋል።

በመርሃ ግብሩ መጨረሻ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ልኡካን ቡድን መሪ አልቫሮ ፒሪስ ፤ “ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ቡድን እና የኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አራተኛው ዙር ግምገማ በባለሙያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ ደርሰዋል” ብለዋል።

ስምምነቱ የሚጸናውና ተፈጻሚ የሚሆነው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ማኔጅመንትና የተቋሙ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በቀጣይ ሳምንታት ውሳኔ ሲሰጡበት መሆኑንም ተናግረዋል።

ወደ ገበያ መር ስርዓት የተሸጋገረውን የውጭ ምንዛሬ ስርዓት ለውጥን ጨምሮ የአገሪቱ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አፈጻጸም በመልካም ጎዳና ላይ የሚገኝ መሆኑንም የቡድኑ መሪ ገልጸዋል።

በተቋሙ የሚደገፈው የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዕድገት እየታየበት መሆኑንና በልዩ ልዩ የኢኮኖሚ መለኪያዎች አንጻር ሲታይ ከሐምሌ 2024 አጋማሽ ጀምሮ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡበት መሆኑንም ተናግረዋል። ይህም ጠንካራ በሆነ የወርቅ፣ የግብርናና የኤሌክትሪክ ምርቶች እየተደገፈ መሆኑን አብራርተዋል።

አዲስ ማለዳ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...