ኢትዮጵያ 1 ሚሊዮን የውጭ ሀገር ስደተኞችን መቀበሏ ተገለጸ

Date:

ኢትዮጵያ 1 ሚሊዮን ስደተኞችን በመቀበል በአፍሪካ ቀንድ ቀዳሚ የስደተኞች መዳረሻ ሀገር ሆናለች ሲል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአሐዱ አስታውቋል።

አሐዱም “ኢትዮጵያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿ በተለያዩ ምክንያቶች ሀገራቸውን ለቀው እየተሰደዱ ባለበት ሁኔታ፤ በዚህ ልክ በሚሊዮን የሚቆጠር የውጭ ሀገር ስደተኞችን መቀበሏ አግባብነት አለው ወይ? ከደህንነትስ አንፃር ለምን በድንበሮችን በቂ ቁጥጥር ማድረግ አልተቻለም?” ሲል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠይቋል።

በመስሪያ ቤቱ የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ማስተባበሪያ የተመላሽ የሴጎች ክትትል መሪ ሥራ አስፈፃሚው አቶ ደረጄ ተጊበሉ በሰጡት ምላሽ፤ “ኢትዮጵያ በዓለማቀፍ ደረጃ የውጡ ሕጎችን ስምምነት በማድረግ ከፈረመቻቸው መካከል ከየትኛውም ሀራት ወደ ሀገሯ የሚገቡ ስደተኞችን የመቀበል ግዴታ እንዳለባት ነው” ብለዋል።

በዚህም መሠረት በተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች፣ በድርቅና ተያያዥ ሰብዓዊ ቀውስ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ለሚሰደዱ የውጭ ሀገር ዜጎች ከለላ እንደምትሰጥ አስረድተዋል፡፡

አክለውም “በድንበር ላይ የሚደረጉ ቁጥጥሮች ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር በቂ የሆነ ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ መታጠቅ አለባት” ሲሉ አስረድተዋል።

ፍልሰትን ለመቆጣጠር በቴክኖሎጂ የበለፀጉ ሀገራት ላይም የወቅቱ ፈተና ሆኖ ይገኛል የሚሉት አቶ ደረጄ፤ ነገር ግን በቀጣይ አቅም በሚችለው መንገድና በዓለማቀፍ ደረጃ በፈረመችው ሕግ በማይጣረሱ መልኩ ድንበሯን ለማስጠበቅ እንደምትሰራ ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያ ስደተኞችን በራሷ አቅም የምትቀበልበት እስካሁን ድረስ አንድም መጠለያ የለም” የሚሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ “የውጭ ሀገር ፍልሰተኞችንም ሆነ የሀገር ውስጥ ፍልሰተኞችን በራሷ አቅም በመጠለያ የማቆየት አቅም ባለመኖሯ ትልቅ ተግዳሮት ከሆኑት መካከል አንዱ ነው” ሲሉ ለአሐዱ ገልጸዋል።

“ይህ በመሆኑ ደግሞ በምጣኔ ሃብት አቅማቸው የበለፀጉ ሀገራት በሚያደርጉት ድጋፍ፤ ኢትዮጵያ መሬቷን ብቻ ለስደተኞች ማቋያ ሰጥታ ትገኛለች” ሲሉ አስገንዝበዋል።

ነገር ግን የውጭ ሀገር ስደተኞችንም ሆነ የሀገር ውስጥ ስደተኞችን ሙሉ በሙሉ እንኳን ባይሆን ተቀብላ የምታስተናግድበትን መጠለያ፤ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ለመገንባት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።

“ይህን ማድረግ ስትችል ደግሞ የሀገሯን ሉዓላዊ ደህንነት ለመጠበቅ ይረዳታል” ሲሉ መሪ ሥራ አስፈፃሚው ለአሐዱ አስታውቀዋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...