ኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አዲስ የባቡር መስመሮችን በመገንባት የሎጂስቲክስ አገልግሎቱን ለማሻሻል እየሰራ በሚገኝበት በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ በኩል መነሻ ባቡር ጣቢያ ከሆነው የሰበታ ባቡር ጣቢያ ጀምሮ እስከ ጅቡቲ ናጋድ ባቡር ጣቢያ ድረስ ያለውን ነባር የባቡር መስመር በፍጥነት የጥገና ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ የአ.ማ ስራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በማህበራዊ ገጻቸው ካሰፉት ጽሁፍ ቅዳሜ ገበያ ተመልክታለች፡፤
ይህም የባቡር መስመሩን ጥራት እና የደህንነት መመዘኛዎችን በተሻለ ደረጃ ለማስቀመጥ ከማገዙም በላይ የባቡር ምልልስና ፍጥነትን ለማሳደገግ ያግዛል ብለዋል፡፡
የጥገና ፕሮጀክቱ የጭነት ባቡሮችን ፍጥነት አሁኑ እየተጓዙበት ከሚገኘው በሰዓት 60 ኪ.ሜ ወደ 67 ኪ.ሜ በሰዓት እንዲጓዙ ያስችላል፡፡
በተመሳሳይ የመንገደኞች ባቡር የጉዞ ፍጥነትን አሁን ካለበት በሰዓት 70 ኪ.ሜ ወደ 90 ኪ.ሜ በሰዓት እንዲደርስ ያደርጋል፡፡
በዚህ የባቡር መስመር ጥገና ወቅት የጥገና ጥራትና ፍጥነት የባቡር መስመሩ አሮጌ ቁሳቁሶች ይወገዳሉ፤ በአዳዲስ ግብአቶች እንደሚካተት አስታውቀዋል፡፡
ባለፉት ስምንት ዓመታት ያለ አገልግሎት ተዘግተው ከነበሩ መስመሮችን ወደ አገልግሎት የማስገባትና የታለመላቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ስራ ይከናወናል ብለዋል፡፡
በአራት ወራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በዚህ የባቡር መስመር ጥገና ፕሮጀክት በሚፈለገው የፍጥነትነና የጥራት ደረጃ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
ቅዳሜገበያ
