የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር የትግራይን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እውነታዎች ከግምት ውስጥ አላስገባም

Date:

 የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በፓርላማ ተገኝተው ያደረጉት ንግግር እንዳሳሰባቸው ገለጹ። የጠ/ሚኒስትሩ ንግግር  በጦርነት በተጎዳው ክልል ውስጥ ያለውን የሰላም ሂደት ሊያዳክም እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። የሃይማኖት መሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ግምገማ “ከህዝቡ የኑሮ ሁኔታ ጋር የሚገናኝ አይደለም” ብለዋል።


የሃይማኖት መሪዎቹ ረቡዕ ባወጡት መግለጫ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቦታው ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እውነታዎች መረዳትን በተመለከተ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ስጋት እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።


የሃይማኖት መሪዎቹ፤ “የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይ ሁኔታ ግምገማ ከሕዝቡ የኑሮ ሁኔታ ጋር የሚገናኝ አይደለም” ሲሉ ገልጸው፤ እንዲህ ያለው አለመጣጣም ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ሊያባብሰው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ተፈናቃዮችን ወደ ቤታቸው የመመለስ ሂደት መሻሻል አለማሳየቱን በመጥቀስ አስቸኳይ ትኩረት የሚሻ አሳሳቢ ውድቀት ነው ብለዋል።


ይህ መግለጫ የመጣው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በ42ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በትግራይ ግጭት እንዳይባባስ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎችን በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገቡ ከጠየቁ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው። “ሌላ ምንም ስራ የላችሁም በፍጥነት ትግራይ ወደ ግጭት እንዳይገባ፣ ወደ ጦርነት እንዳይገባ ስራችሁን አሁን ጀምሩ፤ ከተጀመረ በኋላ ብትናገሩ ዋጋ የለውም” ሲሉ አሳስበዋል።


“የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር የትግራይን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እውነታዎች ከግምት ውስጥ አላስገባም” ሲል የሃይማኖት መሪዎቹ መግለጫው አጽንዖት ሰጥቷል። “ይህ መንግስት የህዝባችንን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለማሟላት ስላለው ቁርጠኝነት ከባድ ስጋቶችን ይፈጥራል” ብሏል።


የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎቹ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የትግራይን ችግሮች በጥልቀት እንዲረዱ እና የሰብአዊ ቀውስና የፀጥታ ስጋቶችን ለመፍታት ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል።
ይህንን የተስተዋለውን ጉዳይ ለመፍታት ቤተክርስቲያኗ የሽማግሌዎች ልዑክ በቀጥታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንዲገናኝ እንደምትልክ አስታውቃለች።

መግለጫው እንደገለጸው፤ የስብሰባው ዓላማ የትግራይን ሕዝብ ስጋት ለማሳየት እና ለሰላም ሂደቱ የበለጠ ምላሽ ሰጪ እና ውጤታማ አቀራረብን ለመደገፍ ነው።  በተጨማሪም፤ “ጠቅላይ ሚኒስትር የተላኩትን ሽማግሌዎች በአክብሮት እንደሚቀበሉ ሙሉ እምነት አለን” ብሏል።

ጠ/ሚኒስትሩ በፓርላማው ንግግራቸው ከሐይማኖት አባቶቹ በተጨማሪም “ባለሃብቶች፣ ዲፕሎማቶች፣ ሙሁራን፣ ኤምባሲዎች አሁን ውጊያ እንዳይጀመር” ሚናችሁን ተወጡ ሲሉ አሳስበዋል፤ “ምክንያቱም ከተጀመረ ከዚህ በፊት የምናውቀው አይደለም ይበላሻል ነገር” ሲሉ ገልጸዋል።

የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች በመግለጫቸው፤ የሃይማኖት ተቋማትን፣ ኤምባሲዎችን፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን እና ለሰላም ቁርጠኛ የሆኑ ሁሉ የትግራይን ሕዝብ ድምፅ እንዲያስተጋቡ  እና የኢትዮጵያ መንግሥት በፕሪቶሪያ ስምምነት የገባውን ቃል እንዲያከብር እንዲያደርጉ አሳስበዋል።አስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...