ከቱሪዝም ዘርፍ 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኘ

Date:

ባለፉት 11 ወራት ከቱሪዝም ዘርፍ 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገለፁ።

በዚህ ዓመት ከቱሪዝም ዘርፉ 5 ቢሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዶ ከዚህ ውስጥ 4.8 ቢሊዮን ብር ማሳካት መቻሉን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

ዘርፉ ማክሮ ኢኮኖሚ ላይ ሶስት በመቶ አስተዋጽኦ ማድረጉን እና በፊት የነበረው አንድ ሚሊየን የማይሞላ ዓመታዊ የቱሪስት መጠን አሁን ላይ ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ገልፀዋል።

ከኮቪድ ጋር ተያይዞ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ የታመቀ የመንቀሳቀስ፣ የመጎብኘትና አዳዲስ ቦታዎችን የማየት ፍላጎት ፈጥሯል ያሉት ሚኒስትሯ፤ በዚህም ዘርፉ ላይ ያለዉን ፍላጎት በማየት በትኩረት በመሰራቱ የቱሪስት ቁጥር መጨመር መቻሉን አንስተዋል።

ቱሪዝም ከጉብኝት በላይ ነው፤ በተዋወቅን ቁጥር አንዱ ስለአንዱ ማሰብ ይመጣል ለጠንካራ ሀገር ግንባታ ቱሪዝም ትልቁን ሚና ይወስዳልም ነው ያሉት ሚኒስትሯ።

እንደ ሀገር ኢንቨስት የሚደረግበት የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ከቱሪዝም መዳረሻነት ባሻገር ሀገራዊ መግባባት ለማምጣት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግም ገልፀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...