የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከነዳጅ ስርጭት ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉ 14 ግለሰቦች ላይ የ12 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ለፖሊስ ፈቅዷል።
- አቶ እስመለዓለም ምህረቱ (የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩ)
ዋና ስራ አስፈጻሚው የተጠረጠሩባቸው ነጥቦች በዋናነት የመንግስትን የነዳጅ ክምችትና ስርጭት ለግል ጥቅም ማዋል ላይ ያተኮሩ ናቸው።
⚫ በሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም ብቻ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ነዳጅ የጫኑ 68 ቦቴዎች (33ቱ የመንግስት እና 35ቱ የግል ኩባንያዎች) ለታለመላቸው መዳረሻ ሳይደርሱ እንዲሰወሩ በማድረግ።
⚫ በቁጥጥር ስር ካልዋሉ ግለሰቦችና የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ጋር በመቀናጀት ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ውጭ እንዲወጣና በኮንትሮባንድ እንዲሸጥ ሁኔታዎችን በማመቻቸት።
- አቶ ዲባራ ፉፋ (የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የነዳጅ ዘርፍ ም/ዳይሬክተር የነበሩ)
ም/ዳይሬክተሩ ስልጣናቸውን ሽፋን በማድረግ በፈቃድ አሰጣጥና በቁጥጥር ስራ ላይ ከፍተኛ ሙስና መፈጸማቸው ተገልጿል።
🔴 የኢንቨስትመንት ፈቃዳቸው ለተቋረጠ፣ ሥራ ላጠናቀቁና ፈቃድ ለሌላቸው ወደ 800 የሚጠጉ አካላት ያለምንም ገደብ ነዳጅ እንዲያገኙ በማድረግ።
🔴 በፀጥታ አካላት የተያዙ የኮንትሮባንድ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎችን “ሕጋዊ ናቸው” የሚል የሐሰት የድጋፍ ደብዳቤ በመጻፍ እንዲለቀቁ በማድረግ።
🔴 መንግሥት ግንባታቸው ለተጠናቀቁ የነዳጅ ማደያ ፈቃድ መስጠቱን እንደሽፋን በመጠቀም አዲስ ለሚከፍቱ የማደያ አገልግሎት እኛ ነን ያስፈፀምነው በሚል እስከ 5 ሚሊየን ብር ድረስ በመቀበል ፍቃድ እንዲያገኙ በማድረግ።
- ከ3ኛ እስከ 14ኛ የተጠቀሱ ተጠርጣሪዎች (የክፍለ ከተማ ባለሙያዎችና የቡድን መሪዎች)
🟢 ተጠርጣሪዎቹ የነዳጅ ምርት ለተጠቃሚው በሕጋዊና በዲጂታል አሰራር መሸጡን የመከታተልና የማረጋገጥ መንግስታዊ ኃላፊነት ተጥሎባቸው ሳለ ይህንን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠር።
🟢 የነዳጅ ምርት በሕገ-ወጥ መንገድ ከቦታ ወደ ቦታ እንዲዘዋወርና በኮንትሮባንድ እንዲሸጥ በማመቻቸት ለድርጊቱ ፈጻሚዎች የሥራ ላይ ሽፋን መስጠት።
🟢 የችርቻሮ ነዳጅ ዋጋ ይጨምራል ተብሎ በሚጠበቅባቸው የወሩ ማብቂያ ቀናት (በተለይም ከየወሩ 24ኛ ቀን ጀምሮ) ማደያዎች ነዳጅ ደብቀው እንዲቆዩና በኮንትሮባንድ እንዲሸጡ በማድረግ ሆን ብለው የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ፤ እነዚህ ማደያዎች በሕግ እንዳይጠየቁና ቁጥጥር እንዳይደረግባቸው በማድረግ በኅብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ እንግልት እንዲፈጠር ምክንያት በመሆን።
🟢 የነዳጅ ሽያጭ በሕጋዊ የዲጂታል ክፍያ (Telebirr/CBE Birr) እንዳይፈጸም በማድረግ፣ የገንዘብ ዝውውሩ ከፋይናንስ ሥርዓት ቁጥጥር ውጪ እንዲሆን በማድረግ፤ በዚህም ከታኅሳስ 30 እስከ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ባለው አንድ ወር ውስጥ ብቻ ከ 2.6 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ነዳጅ በኮንትሮባንድ እንዲሸጥ በማድረግ መንግሥት ማግኘት የሚገባውን ገቢ እንዲያጣ በማድረግ፤
🟢 ከአዲስ አበባ ነዳጅ ጭነው ወደ ክፍለ ሀገር የሚሄዱ ከባድ ተሸከርካሪዎች ነዳጅ እንዳያገኙ የሚከለክሉ “ሕገ-ወጥ የሰርኩላር ደብዳቤዎችን” በመጻፍ መጉላላት እንዲፈጠር በማድረግ፤ … ተወንጅለዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ለችሎቱ ምንም አይነት ወንጀል አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው ተከራክረው የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።
ፍ/ቤቱ ፖሊስ ለጀመረው ምርመራ ስራ ተጨማሪ የ12 ቀን ጊዜ ፈቅዷል።
