ከጥር 3 እሰከ ጥር 12/2018 ዓ.ም ደረቅ እና ቀዝቃዛ አየር ይኖራል

Date:

ከጥር 3 እሰከ ጥር 12 ቀናት ከሳይቤሪያ ከፍተኛ የአየር ግፊት ላይ በመነሳት ወደ ሀገራችን የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛ አየር እንደሚኖረው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን፤ የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ  በተለይም በሰሜን፣ ምስራቅ፣ መከከለኛዉና ደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በመካከለኛዉ፣ ምሥራቅ፣ በመካከለኛዉ እና የደቡብ ደጋማ ቦታዎች ላይ የለሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከአምስት (5) ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ። 

በሌላ በኩል በጸሀይ ኃይል ታግዘው የሚፈጠሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ጋር ተያይዞ በመጨረሻዎቹ ቀናቶች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡

ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብ አሮሚያ ዞኖች፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች እና ጥቂት የደቡብ ሶማሌ ዞኖች ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በተጨማሪም በሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት ወቅቱን ያልጠበቀ አነስተኛ መጠን ያለዉ ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...