የኤርትራ መንግስት የዘር ማጥፋት እያደረሰ ነው ሲል የቀይ ባህር አፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ከሰሰ።
የቀይ ባህር አፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅት በኤርትራ መንግስት እየተፈጸመ ነው ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም የቀይ ባህር አፋር ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር ኢብራሂም አሮን፥ የኤርትራ መንግስት ከ 1993 ጀምሮ በኤርትራ አፋር ህዝቦች ላይ የጀመረው የዘር ማጥፋት ወንጀል አሁንም ተባብሶ መቀጠሉን ተናግረዋል ።
የኤርትራ መንግስት በቀይ ባህር አፋር ዝህቦች ላይ የዘር ማጥፋት፣ ማሳደድ እና ማፈናቀልን ጨምሮ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ ነው ያሉት የድርጅቱ ለቀመንበር ፥እየደረሰ ያለው ግፍ እንዲቆምና አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
በኤርትራ አፋር ህዝቦች ላይ እያደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ ለአፍሪካ የሰብአዊ እና ህዝባዊ መብቶች ኮሚሽን ባለ 120 ገጽ የቅሬታ ሰነድ ማቅረቡን የገለጸው ድርጅቱ፥ ያቀረብነው ቅሬታ በ60 ቀናት ውስጥ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ሲል ጠይቋል።
አሁንም በኤርትራ አፋር ህዝቦች ላይ እየተፈጸመ ያለው ያለው ዘር ማጥፋት ወንጀል፣ በሴቶች፣እናቶችና ህጻናት ላይ እየተፈጸመ ያሉ ጾታዊ ጥቃቶች እንዲሁም የቀይ ባህር አፋር ህዝብን ማሳደድና ማፈናቀል ሊቆም ይገባልም ሲል ድርጅቱ አሳስቧል።
የአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንመሰ ፥ በቀይ ባህር አፋር ህዝብ ላይ በኤርትራ መንግስት የደረሰውን ጅምላ ግድያና እስር እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተመለከተ ያቀረብነውን ሰነድ ተመልክቶ ዓለማቀፋዊ እውቅናናአፋጣኝ ምላሽ ሊሰጥልን ይገባል ሲልም ድርጅቱ ጠይቋል።
በአትዮጵያ ብቻ ከ60 ሺ በላይ የተመዘገቡ እና ከ 40 ሺ በላይ ያልተመዘገቡ የቀይ ባህር አፋር ስደተኞች እንደሚገኙ የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ይገልጻል።
