ከ1ሺህ በላይ ተፅእኖ ፈጣሪ የስራ ሀሳቦች በመረጃ ቋት ዉስጥ እንደተመዘገቡ ተገለፀ

Date:

የስራ ሀሳቦቹን ወደ ተግባር ቀይሮ ለመቀጠል ግን የሀገር ዉስጥ ባለሀብቱ ፍላጎት እያሳየ አይደለም ተብሏል።

በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ስር የሀሳብ ባንክ በተባለ የምዝገባ ስርአት ዉስጥ አዳዲስ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀሳቦችን መመዝገቡን ሰምተናል።

ሆኖም በመረጃ ቋቱ ያሉትን ሀሳቦች መሬት ለማዉረድ ክፍተቶች አሉ ተብሏል።

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የስራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ በሀገርአቀፍ ደረጃ ተወዳድረዉ ያሸነፉ ብቁ የስራ ፈጠራዎች የጎረቤት ሀገራት ባለሀብቶች ተመርጠዉ ወደ ቢዝነስ እየተቀየሩ መሆኑን ገልፀዋል።

በሀገር አቀፍ ዉድድሮች ችግር ፈቺነታቸዉ ታምኖበት የተመረጡ ሀሳቦችን የግል ዘርፉን እገዛ የሚጠይቅ እየሆነ ነዉ ተብሏል።

የሚኒስትር መስሪያ በቤቱ በተለይም ለክልሎች ለአዳዲስ የስራ ፈጠራ ሃሳቦች መሰረታዊ ድጋፍ እንዲረግ እየጠየቀ ነዉ የሚሉት ሚኒስትር ዴኤታዉ ሆኖም በባለሀብቱም በኩል ይህንን እያገዘ አይደለም ብለዋል።

አሁንም የክህሎት ልማት ዉድድር እያከናወነ ነዉ የሚሉት አቶ ሰለሞን ሶካ የቴክኖሎጂ መፍትሔ ያላቸዉ ሀሳቦችን እይታ እንዲኖራቸው ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል።

የስራ ፈጠራ ውድድሮች ከውጤታማነት እና ቀጣይነት አኳያ ውስንነቶች እንዳሉባቸው ይነሳል።

በተለያዩ አካላት የሚዘጋጁ የስራ ፈጠራ ውድድሮች እየተበራከቱ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ከውጤታማነት እና ቀጣይነት አኳያ ሲታዩ ግን ከፍተኛ ውስንነት እንዳለባቸው በተደጋጋሚ ይገለፃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...