ከ100 ኪግ በላይ ካናቢስ በመኖሪያ ቤት ውስጥ የሸሸጉ ተጠርጣሪዎች በቁጥር ስር ዋሉ

Date:

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በቅድመ ወንጀል መከላከል በጥናት ላይ ተመስርቶ ባማናወነው ክትትል ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 7፡40 ሠዓት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አጂብ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በተደረገ ፍተሻና ብርበራ ከ100 ኪሎ ግራም በላይ ካናቢስ የተሰኘን አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ሊያውል መቻሉን አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ አሸብር መኮንን እና ስብሀቱ አያሌው የሚባሉ ሲሆኑ የተጠቀሰውን አደንዛዥ ዕፅ አምስት አምስት ኪሎ በሚይዡ ከረጢቶች በመጠቅለል ወደ ገበያ ለማቅረብ ሲያዘጋጁ እንደተያዙም ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተጨማሪ ምርመራ የማስፋት ተግባሩን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ተገቢውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማጠናቀር ክስ እንደሚያስመርትም ገልጿል፡፡

አደንዛዥ ዕፆችችን ማምረት፣ መስራት፣ ማዘዋወር ወይም መጠቀም የወንጀል ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 525 ላይ በግልፅ የተደነገገና በወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር መሆኑን ሁሉም ልብ ሊለው የሚገባ ከመሆኑም በላይ እነዚህን እና መሰል ዕፆችን ሲጠቀም፣ ሲያዘዋውር፣ ሲሸጥና ሲጠቀም የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብም ይሁን ቡድን ላይ በህጉ መሰረት ጠበቅ ያለ ርምጃ እንደሚወስድም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያሳስባል፡፡

ምንጭ:- አአ ፖሊስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...