“የሱዳን ኤል ፋሸር ነዋሪዎቹ ከእንስሳት መኖ እና የቆሸሸ ምግብ እየበሉ ነው” የአለም ምግብ ፕሮግራም/WFP/
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በከተማዋ በሱዳን ጦርነት ሳቢያ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ተፈጥሯል ብሏል። በዚህም ሳቢያ የኤል ፋሸር ነዋሪዎች የእንስሳት መኖ እና የቀሸሸ የምግብ ተረፈ ምርት መመገብ በህይወት ለመቆየት የቀራቸው ብቸኛ አማራጭ መሆኑን ነው ድርጅቱ ያሳወቀው።
ድርጅቱ ወደ 250,000 ለሚጠጉ ሰዎች ምግብ እንዲገዙ የዲጂታል እርዳታ ድጋፍ ቢያቀርብም በገበያ ላይ የሚቀረው ምግብ እየቀነሰ እና ፍላጎቱ እየጨመረ መጥቷል ብሏል።
በከተማዋ የተከሰተው ዓይነት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ፍላጎት መቼም ተከስቶ አያውቅም ያለው WFP ባለጅርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ተማጽኗል።
