“ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት ታቅዷል” – ቡናና ሻይ ባለስልጣን

Date:

በ2018 የስራ ዘመን ከቡና፣ ሻይና ቅ/ቅመም ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት መታቀዱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ የቡና ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 470ሺህ ቶን ቡና በመላክ ከ2.65 ቢሊየን ዶላር በላይ የተገኘበት መሆኑ መገለጹ ይታወሳል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዕቅድ በተገመገመበት ወቅት እንደገለጹት፥ በተያዘው በጀት ዓመት ከ600ሺህ ቶን ቡና ለገበያ በማቅረብ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት ታቅዷል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ለክልል የስራ ኃላፊዎች ባቀረቡት ጥሪ፤ EUDR/ አውሮፓ ህብረት ያወጣውን ከደን ጭፍጨፋ ነጻ የሆነ ምርት የመግዛት መመሪያ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ፣ በሳይንሳዊ መረጃ ላይ የተመሰረተ፣ በጥራትም ሆነ በመጠን ከፍ ያለ ቡና ወደ ገበያ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...