በአርቲስ ስዩም ተፈራ የተፃፈው ‘ሐሙስ’ የተሰኘው ቴአትር የፊታችን ሐሙስ ለእይታ ይበቃል ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለእይታ የሚበቃው ይህ ቴአትር ተክሌ ደስታ እና ተስፋዬ ሲማ አዘጋጅተውታል ።
ቴአትሩ በ8:00 ሰዓት ለእይታ ይቀርባል።
ቴአትሩን ፕሮዲዩስ አድርጎ ያቀረበው እውቁ የፊልም ባለሙያ @sewmehon Yismaw ነው ።
ሰው መሆን ከዚህ ቀደም በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በ’ባሎች እና ሚስቶች ‘ ቴአትር 360ዲግሪ የሚሽከረከር መድረክ ግንባታ እውን እንዲሆን ያደረገ የቴአትር አፍቃሪ ነው ።
