ከሰሜኑ ጦርነት መልስ የተረጋጋ የሠላም ሁኔታ ሳይፈጠር በተለያዩ አካላት የሚደረጉ ወታደራዊ ይዘት ያላቸው ዝግጅቶች፣ ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮችና የሚዲያ ዘመቻዎች እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አስታውቋል፡፡
የሰብአዊ መብት ተቋሙ ባወጣው መግለጫ፤በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በትግራይ የታጠቁ ኃይሎች መካከል ከ2013 እስከ 2015 ዓ.ም በዘለቀው ጦርነት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸማቸውንና በዜጎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅሎች መፈጠራቸውን አስታውሷል፡፡
ጦርነቱ በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ቢቋጭም፣ የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ ከሁለት ዓመት በኋላ፣ የስምምነቱ ቁልፍ ጉዳይ ሳይተገበር የዳግም ግጭት ስጋት ማንዣበቡ እጅግ አሳሳቢ ነው ብሏል፤ ተቋሙ።
የቀድሞ ታጋዮችን ትጥቅ ሙሉ በሙሉ የማስፈታት፣ የመበተንና የማቋቋም ሂደት መጓተት፣ የኤርትራን ጨምሮ ሌሎች ኃይሎች ከትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ አለመውጣት፣ እንዲሁም በሚሊዮን የሚቆጠሩ የውስጥ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው አለመመለሳቸው የሰላሙን ሂደት አደጋ ላይ ጥሎታል ይላል፤ በመግለጫው፡፡
መንግሥት በትግራይ ክልልና አካባቢው ያለውን ግጭት ቀስቃሽ እንቅስቃሴን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ኢሰመጉ ጠይቋል፡፡
አክሎም፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ሀይሎች፣ አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ተገቢውን ጥረት እንዲያደርጉና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑና የአካባቢውን ማህበረሰብ ስጋት ውስጥ ከሚከቱ እንቅስቃሴዎችእንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡
የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሚዲያዎች፥ ምሁራን እንዲሁም የፖለቲካ ድርጅቶች ሰላምን በማስፈን ረገድ የበኩላቸውን እንዲወጡ ኢሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡