መንግሥት፣ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች እንደየአገልግሎታቸው ዓይነት “ወጥ ቀለም” እና መለያ ኮድ እንዲኖራቸው እቅድ መያዙን ተሰምቷል።
የተሽከርካሪዎች ቀለምና መለያ ኮድ ከከተማ ከተማ የተለያየ ይሆናል ተብሏል።
የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪ ተሽከርካሪዎች ሹፌሮችም፣ ወጥ የደንብ ልብስ እንዲለብሱ ለማድረግ እቅድ እንደተያዘ ተነግሯል።
የትራንስፖርት ሚንስትር ዓለሙ ስሜ፣ ያረጁ ተሽከርካሪዎችን ከሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ውጭ ለማድረግ እንደተወሰነ ሰሞኑን ባንድ ስብሰባ ላይ መናገራቸው መዘገቡ ይታወሳል።
