የመምህር ዘለዓለም ወንድሙ የአሸኛኘትና የስንብት መርሐ ግብርን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫው
“እመኒ ሐየውነ ወእመኒ ሞትነ ለእግዚአብሔር ንሕነ።”
“እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን።” ሮሜ 14÷8
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ እንዳለ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ በክርስቶስ ኖሮ ከክርስቶስ ጋር ለመኖር ናፍቆ የሄደውን የወንድማችንን እና የመምህራችንን ዘለዓለም ወንድሙን እንዲህ እንሸኘው ይኼንን ጋዜጣዊ መግለጫ እንሰጣለን።
መምህራችን መምህር ዘለዓለም ወንድሙ የእረፍት ዜናው ከተሰማበት ጊዜ አንስቶ መላው ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ በጥልቅ ሐዘን ውስጥ ገብተዋል። መምህር ዘለዓለም ወንድሙ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን በታማኝነት ያገለገለ የሕይወት ዘመኑን ሙሉ መልካም የሆነ፤ ክርስቲያናዊ ጠባዩን ያልቀየረ ለብዙዎቹ ምሳሌና አርአያ ሆኖ የኖረ የወንጌልን ችቦ በመላው ዓለም ያቀጣጠለ ታላቅ መምህር ነው ።
ስለዚህ ይኼንን ወንድማችንን በልዩ ስነ ሥርዓት የሕይወት ዘመን መልካም አገልግሎቱን ታሳቢ በማድረግ እና የቤርስቲያኒቱን ክብር በሚመጥን መልኩ በታላቅ የአሸኛኘት ስነ ሥርዓት ለመሸኘት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ይሁንታ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሥራዎችን ሲሠራ ቆይቷል።
ከዚህ በመነሳት የአሸኛኘት ስነ ሥርዓቱ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጀምሮ እስከ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ድረስ ስርዓቱን የጠበቀ ይሆን ዘንድ አሸኛኘቱ የሚከተሉትን ሂደቶች የሚከተል መሆኑን እናሳውቃለን።
- የመምህር ዘለዓለም ወንድሙ አስከሬን ረቡዕ መጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ ም ከአሀገረ አሜሪካ ተነስቶ ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርግ ይሆናል።
- ሐሙስ መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ ም አስከሬኑ ከጠዋቱ 12 :00 ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ይደርሳል።
- በዛም በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እየተመራ የወንድማችን ወዳጅ ዘመዶች የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት ሊቃውንት ጥቅ ድርባቸውን ለብሰው አቀባበል የሚያደርጉለት ይሆናል። በቦሌ ዓለም አቀፍ ማረፊያ የሚገኙት የተመረጡ እና ፈቃድ የተሰጣቸው አካላት ብቻ ናቸው።
- ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ ከብሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ጀምሮ እስከ ቦሌ ደ/ሳሌም መድሐኔዓለም ድረስ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን እና በምእመናን ታጅቦ ወደ ቦሌ ደ/ሳሌም መድሐኔዓለም ካቴድራል ጉዞ ያደርጋል።
- በቦሌ ደብረ ሳሌም መድሐኔዓለም ካቴድራል አጭር ቆይታ ካደረገ በኋላ ቀጥታ በመለከት ድምጽ ነጋሪት እየተጎሰመ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቃውንት በመምህራነ ወንጌል በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣት ዘማርያን እና በበርካታ ምእመናን ታጅቦ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ መስቀል አደባባይ ይደረሳል።
- ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የተለያዩ የአሸኛኘት መርሐግብሮች የሚከናወኑ ሲሆን በዚህም ቦታ
ከጠዋቱ 5:00 – 8:00 ሰዓት ድረስ የተለያዩ ክንውኖች ይኖሩናሌ። እነዚህም:-
ከጠዋቱ 5:00 – 5:30 የመርሐ ግብር መክፈቻ እና ጸሎት
ከ5:30 እስከ 6:00 ያሬዳዊ ዝማሬ የዘማርያን ኅብረት ዝማሬ እና ቅኔ ይቀርባል
ከ6:00 – 6:15 የመምህር ዘለዓለም ወንድሙ የሕይወት ታሪክ በንባብ ይቀርባል
6:15 – 6:40 ከተለያዩ ተቋማት የሚቀርቡ የስንብት መልዕክቶች ይቀርባሉ
ከ6:40 – 7:00 ከቤተሰብ እና ከወዳጅ ዘመዶች ስለወንድማችን የሚቀርቡ ምሥክርነቶች በተለያዩ አካላት ይሰጣል።
ከ7:00 – 7:30 የወንጌል መርሐ ግብር
ከ7:30 – 7:40 በሰንበት ትምህርት ቤቶች እና በዘማርያን የጋራ ዝማሬ ይቀርባል።
ከ7:40 – 8:00 ቃለ ምእዳንና ቡራኬ በብፁዓን አባቶች ይሰጣል
ከቀኑ 8:00 ላይ የመስቀል አደባባዩ መርሐ ግብር ተጠቃሎ ጉዞ ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ጉዞ የሚያደርግ ሲሆን ከቀኑ 9:00 ላይ አጭር ጸሎት ተደርጎ ሥርዓተ ቀብሩ የሚፈጸም ይሆናል።
የተወደዳችሁ ይኼንን ጋዜጣዊ መግለጫ የምትሰሙ እና የምትመለከቱ ሁሉ ወንድማችንን የምንሸኘው በታላቅ መንፈሳዊ ስነ ሥርዓት ከፍ አድርገን ሲሆን የአለባበስ ሁኔታችንም በተመለከተ መምህር ዘለዓለም ወንድሙ የዕለቱ ሰማያዊ ሙሽራችን ስለሆነ ሁላችንም ነጭ ልብሳችንን ለብሰን እንሸኘዋለን።- ስለዚህ የተወደዳችሁ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መምህራነ ወንጌል፣ ዘማርያን እና ምእመናን በሙሉ በዕለቱ ነጭ ልባሳችንን በመልበስ በቦታው በመገኘት በታላቅ መንፈሳዊ ስነ ሥርዓት እንድንሸኘው በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን ስም ከወዲህ ለማሳሰብ እንወዳለን።
ክብሩን የሚመጥን ሐውልት ለማሰራት የጀመረውን በጎ ሥራዎች ለማስቀጠል በስሙ ለሚቋቋመው ፋውንዴሽን የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ
Dsk Mariam Zell # 202-391-5952
የዜል አካውንት
+++
1000751862192
CBE
Abreham and Eliyas and Dawit
+++
https://gofund.me/f90c35e5f
