የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከመጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ተመን ይፋ አደረገ።
በዚህ አዲስ ማሻሻያ መሠረት በሁሉም የነዳጅ አይነቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ የታየ ሲሆን፣ ዝርዝሩም እንደሚከተለው ቀርቧል፦
አዲሱ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ፡
ቤንዚን : 132 ብር ከ18 ሳንቲም
ነጭ ናፍጣ : 139 ብር ከ84 ሳንቲም
ኬሮሲን : 146 ብር ከ14 ሳንቲም
የአውሮፕላን ነዳጅ : 145 ብር ከ23 ሳንቲም
ቀላል ጥቁር ናፍጣ: 137 ብር ከ03 ሳንቲም
ከባድ ጥቁር ናፍጣ: 133 ብር ከ45 ሳንቲም
ማሳሰቢያ፦ ይህ አዲስ ዋጋ ከመጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አሳስቧል።
