የመድረክ መሪና ጋዜጠኛ ወንድወሰን ከበደ መጽሐፍ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እየመጣ ነው ። እሁድ፣ November 30 ቀን 2025 ዓ.ም ከቀኑ 3፡00pm ሰዓት ጀምሮ ስፕሪንግ ፊልድ ፣ ቨርጂኒያ በሚገኘው፣ በዋተር ፎርድ ኤቨንት ሴንተር አዳራሽ ውስጥ ከልዩ ጥበባዊ ዝግጅት ጋር ይመርቃል።
መጽሐፉ ከአዲስ አበባ እስከ ሰሜን አሜሪካ ለ25 ዓመታት ያዘጋጃቸውን እና የመራቸውን የጥበብ መድረኮች የዳሰሰበትና የዘመን መልኮቹን ያስቃኘበት ነው፡፡
በእለቱ ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር የተጋራቸውን ታሪኮችና ትዝታዎች ጣዕማቸው ሳይደበዝዝ በልዩ ሁኔታ ተከሽነው ይቀርባሉ።
