የረባ መቀመጫ በሌለበት ት/ቤት በሚማሩ ተማሪዎች፤ የረባ ደመወዝ ሳይከፈለው በሚያስተምር መምህር የሚመጣው ምን እንደሆነ ማጥናት ያስፈልጋል

Date:



ለ34 ዓመት በመምህርነት ካገለገሉ በኋላ ወደፖለቲካው መለስ ያሉት የኢሕአፓው አበበ አካሉ ፓርቲያቸውን ወክለው ሳይሆን አንጋፋ መምህርነታቸው ተንተርሰው ስለየ12ኛ ክፍል ውጤት አስተያየት ሰጥተውናል፡፡

ምን አሉ ?

” ኩረጃን ለማስቀረት የተወሰዱ እርምጃዎች ይበል የሚያሰኙ ናቸው፡፡ ግን በዚህ ደረጃ አራቱን ተከታታይ ዓመታት ተማሪ ሲወድቅ ምንድን ነው ችግሩ ? ብሎ ወደ ውስጥ መመልከት ተገቢ ነው፡፡

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ወላጆች ት/ቤቶችን እንዲጠይቁ ብለዋል፡፡ ይሄ ውድቀት ከየት ወጣ ብሎ ማጥናትና ት/ቤቶችን መጠየቅ ያለበት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንጅ ወላጆች አይደሉም፡፡

5.2% ያላሳለፉት የመንግስት ት/ቤቶች ናቸው፡፡ ብዙ ቁጥር ያለው ተማሪም የሚገኘው መንግስት ት/ቤት ነው፤ ስለዚህ ት/ቤቶች ያላቸው አደረጃጀት መፈተሽ አለበት፡፡ ለምንስ ነው የመንግስት ት/ቤቶች በዚህ ልክ ወርደው 5.2% ተማሪዎችን ያሳለፉት?

ባለስለጣናት የራሳቸውን ልጆች በኢንተርናሽናል ት/ቤቶች እያስተማሩ ድሃውን ልጅ በመንግስት ት/ቤቶች መሞከሪያ አድርጎ በዚሁ እንቀጥላለን ማለት ተማሪ ወደ ትምህርት ዓለም እንዳይመጣ መግፋት ነው፡፡

በአንድ ክፍል 80እና 90 ተማሪዎች ተቀምጠው፣ በአንድ ወንበር አራት ተማሪዎች እየተጣበቡ ተምረው የተሻለ ውጤት መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡

የትኛው ላብራቶሪና መርጃ መሳሪያ ያለበት ት/ቤት አለውናነው? የረባ መቀመጫ በሌለበት ት/ቤት የሚማሩ ተማሪዎች፤ የረባ ደመወዝ ሳይከፈለው በረሃብ አለንጋ እየተጠበሰ በሚያስተምር መምህር የሚመጣው ምን እንደሆነ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡

91 መቶ የወደቁ ተማሪዎች መጨረሻቸው ምንድን ነው የሚሆነው ?ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ማጠንከር የሚገባቸው የ12ኛ ክፍል ፈተናን ብቻ አይደለም፡፡ ከኬጂ ጀምሮ የትምህርት ጥራቱን ማስጠበቅ ይገባቸዋል ” ብለዋል፡፡

የጸጥታው ችግር በተመለከተስ ምን አሉ ?

” ለትምህርት አንዱ ትልቁ እንቅፋት ጦርነት ነው፡፡ የጥይት ጩኸትና የመምህሩን ድምጽ እየሰማ የሚማር ተማሪ ምን አይነት የትምህርት ትኩረት ይኖረዋል? የሚለው ነገር በጣም አሳሳቢ ነው፡፡

በአማራ ክልል ጦርነት በኦሮሚያ ክልል የሰላም እጦትና በትግራይ ክልል ባለው ችግር ተማሪዎቹ አብዛኛውን ወራት አይማሩበትም፡፡ አንድ መምህር 45 ደቂቃን ለአራት ከፍፍሎ ነው ከዓመታዊ እቅዱ ጋር አጣጥሞ አስተምሮ የሚወጣው፣ ይህን ለማድረግ ደግሞ የሰላም አየር ያስፈልጋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ውስጥ ተቀምጦ በየአካበቢው የሚታይ የሰላም እጦት ችግር  አንዱ የተማፊዎች ውጤት ማዘቅዘቅ ምክንያት ነው ተብሎ ሊገለጽ ያስፈልገዋል፡፡

የሰላሙ ችግር የትምህርት እንቅፋት ሆኖ እያለ፣ ት/ቤቶች ወድመው፣ ተማሪዎች ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለው እየተማሩ ባሉበት ሁኔታ የተሻለ ውጤት ይመጣል ብሎ ማሰብ ከንቱ ነው፡፡ ይህ ሳይስተካከል ተማሪው ላይ ብቻ መፍረድም ተገቢ አይደለም፡፡

ጸጥታው የተከበረ የመማሪያ ስፍራ መፍጠር የመንግስት ኃላፊነት ነው፡፡ ዘንድሮ የተፈታኝ ተማሪዎች ቁጥር ቀንሷል፡፡ ለምን እንደቀነሰ መጠናት አለበት፣ የሚፈተነውና ወደ ት/ቤት የሚሄደው ተማሪ ብዛት በየዓመቱ መጨመር ነው ያለበት፡፡

ቁጥራቸው እየቀነሰ ያለው ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እየተለዩ ስለሆነ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

መፍትሄውን በተመለከተስ ምን አሉ?

” የትምህርት ስርዓት ግቡ ተማሪዎችን በፈተና አጨናንቅ መጣል አይደለም። የፈተናን መውጫና መግቢያን ብቻ በማብዛት የትምህርት ጥራትን ማምጣት አይቻልም፡፡ ፕ/ር ብርሃኑ በኢትዮጵያ የትምህርት አውድ ከታች ጀምሮ ያለውን አውድ አያውቁትም፡፡ ኢትዮጵያ የኖሩበት ጊዜ በጣም ጥቂት ነው፡፡

ስለዚህ የፈላ ውሃ ጠጥቶ ሲያስተምር ከነበረው መምህር ተሞክሮ መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡ የትምህርት ጥራት የሚመጣው በፈተና ብዛት አይደለም ከኬጅ ጠንክሮ በማስተማር ነው፡፡

ልጆችን በእውቀት ኮትኩተን የምናሳድገው እንዴት ብናስተምራቸው ነው ? ምን አይነት የትምህርት ግብዓቶች ያስፈልጋሉ ? የሚለውን መፈተሽና ስርዓተ ትምህርቱን መከለስ ያስፈልጋል፡፡

ባጣ ቆየኝ የሆነውን የመምህርነት የሥራ መስክንም ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል፡፡ መምህሩ ላይ በሚሰራው ሥራ ነው ውጤቱን ተማሪው ላይ ማየት የሚቻለው ” ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡


@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...