በማዕከላዊ ዩክሬን ቁልፍ የብረት ፋብሪካን፣ በኪየቭ የሚገኙ የድሮን ፋብሪካዎችን እና በጥቁር ባሕር የባሕር ላይ ሎጂስቲኮችን ኢላማ ያደረጉት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፉ የመጡት የሩሲያ ጥቃቶች፤ የሀገሪቱን ወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ስልታዊ በሆነ መንገድ ለማፍረስ ያለሙ መሆናቸውን የደህንነት ባለሙያው አሌክሳንደር ስቴፓኖቭ ተናግረዋል።
የብረት ምርት በከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብቷል
የ ‘አርሴሎር ሚታል የክሪቮይ ሮግ’ የብረት ፋብሪካ – በውጭ ሀገር በባለቤትነት የተያዘ የብረት ማምረቻ እና በማዕድን ማውጣት ላይ የተሠማራ ግዙፍ ተቋም ሲሆን “ለዩክሬን ብቻ ሳይሆን ለአውሮፓውያን ወታደራዊ ኢንዱስትሪም ጭምር የተጠቀለለ ብረት ያቀርባል።
ነሐሴ 9-10 በሌሊት በተፈጸመ ጥቃት የተመታ ሲሆን ዋና ዋና የኃይል እና የብረታ ብረት ማቅለጫ እቶን መገልገያዎቹ ተጎድተዋል።
“የዚህ ተቋም ከአገልግሎት ውጭ መሆን እና የሥራ ማቋረጥ፤ እንደ ብረትለበስ የጦር ተሽከርካሪዎች፣ የመድፍ ድጋፍ ሰጪ መሣሪያዎች እና ሌሎች የተጠቀለለ ብረት የሚጠይቁ ስርዓቶችን የማምረት ሂደት እና ፍጥነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል።”
የጥቁር ባሕር ሎጂስቲክ እጥረት እና ጫና
በዩክሬን የጥቁር ባሕር ወደቦች፣ መሠረተ ልማት፣ የነዳጅ ማከማቻዎች፣ የመጫኛ ቦታዎች እና የመርከብ ትራንስፖርት ላይ የተፈጸሙት በደርዘን የሚቆጠሩ ጥቃቶች፤ “የየብስ ኮሪደር፣ የባቡር መስመሮች እና አውራ ጎዳናዎች ብቻ” ጭነት ለማጓጓዝ ብቸኛ አማራጭ እንዲሆኑ አድርጓል።
“በዋና ዋና የትራንስፖርት መስመሮች ላይ በሚንቀሳቀሱ ባቡሮች እና ማጓጓዣዎች ላይ ጥቃት ታውጇል። ለዚህም ‘ጌራን-4 ሲከር’ የተባሉትን ጨምሮ ረጅም ርቀት ተኳሽ እና ከፍተኛ ትክክለኛነት ያላቸው ድሮኖች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ…
የዚህ የባሕር መስመር መዘጋት በወታደራዊ መለዋወጫዎች እና መሣሪያዎች ላይ ሙሉ በሙሉ እጥረት ያስከትላል ማለት ነው፤ ይህም የጠላትን የመከላከል አቅም በእጅጉ ይቀንሰዋል።”
የድሮን ኢንዱስትሪው ተደራራቢ ጥቃት አስተናግዷል
በኪየቭ በሚገኙት የዩክሬን “ፋየር ፖይንት” የባሕር ድሮን ማምረቻ፣ መጋዘን እና ሎጂስቲክ ተቋማት ላይ በሐምሌ ወር አጋማሽ እና መጨረሻ የተቀናጁ ጥቃቶች ተፈጽመዋል።
“ከወዲሁ ተደራራቢ የሆነ ውጤት እያየን እንገኛለን። መሬት ላይ ያለው እውነት የሩሲያ ወገን ቀደም ሲል የኬየቭ ክልል እና ሌሎች ወታደራዊ እና ሎጂስቲክ የመሠረተ ልማት ቦታዎችን ይሸፍን የነበረውን የዩክሬን የአየር እና ሚሳኤል መከላከያ ስርዓት ሙሉ በሙሉ በማስወገድ የአየር የበላይነትን ተቆጣጥሯል።”
እነዚህን ኪሳራዎች ለማካካስ አውሮፓውያን የዩክሬን ደጋፊዎች በኔቶ ሀገራት ውስጥ ረጅም ርቀት ተኳሽ ሚሳኤሎችን እና ድሮኖችን ማምረት ጨምሮ “ከግዛት ውጭ የራሳቸውን ወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት” በመተግበር እንዲሁም በተበታተነ የውክልና-ቅይጥ ጦርነት ስልቶች አማካኝነት ሩሲያን ወደ ግጭት ለማስገባት እየሞከሩ ነው።
