የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል መጋቢት 18 እና 19 ይከበራል

Date:

የዚህ በአል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን  የሲዳማ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

የሲዳማ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ወሰንየለህ ስምኦን ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት የፍቼ ጫምባላላ በዓል በውስጡ ያሉ እሴቶች  የህብረተሰቡን መወዳጀትን ሁሌም የሚያጠናክር በመሆኑ በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ብቻ ሳይሆን ሁሌም መጠበቅና ባህል ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።

ፍቼ ጫምባላላ በዓል በኢትዮጵያ ደረጃ ከፌዴራልና ከሁሉም ክልሎች እንዲሁም ከውጪ ሀገራት በርካታ ታዳሚዎች ተገኝተው የሚያከብሩት ታላቅ በዓል መሆኑን አቶ ወሰንየለህ በመግለፅ እነዚህን እንግዶች ታሳቢ ባደረገ መልኩ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉንና ገልፀዋል።በዓሉ ያለምንም ጸጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር በተለያዩ ጸጥታ አካላት በኩል አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጋል ።

የበዓሉ አከባበር መጋቢት18 በሀዋሳ ሲዳማ ባህል አዳራሽ እንዲሁም የካቲት 19 ቀን2017 በሶሬሳ ጉዱማሌ በተለያዩ ባህላዊ ዝግጅቶች ከተከበረ በኋላ በቀጣይ ለሁለት ሳምንታት በክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች በልዩ ልዩ ደማቅ ዝግጅቶች ይቀጥላል ተብሏል።የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል በዩኔስኮ ከተመዘገበ ዘንድሮ 10ኛ አመቱ መሆኑም ተነግሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...