የባሕር በር ጥያቄ የመንግሥት ፖለቲካዊ ፍላጎት ተደርጎ መወሰድ የለበትም

Date:


የባሕር በር ጥያቄ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ እንጂ የመንግሥት ፖለቲካዊ ፍላጎት ተደርጎ መወሰድ የለበትም ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ሙሉዓለም ሀይለማርያም ተናገሩ።

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ሙሉዓለም እንደገለፁት፤ የባሕር በር ጥያቄ የብሔራዊ ጥቅም እንጂ የመንግሥት ፍላጎት ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም።

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር መሰረታዊ ከምትላቸው የብሔራዊ ጥቅም አጀንዳዎች መካከል አንዱ የሆነውን የባሕር በር መልሶ የማግኘት ጉዳይ ከዘላቂ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ጋር ብቻ ተያይዞ መታየት ያለበት እንደሆነ ገልፀዋል።

እያደገ የመጣውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና የህዝብ ቁጥር ሊሸከም የሚችል መሰረተ ልማት ካልተገነባ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ አፍኖ ማቆየት የሚቻልበት ሁኔታ የለም፤ ከዚህ አኳያ ሀገሪቱ የምታስተዳድረው የባሕር በር ከምንጊዜውም በላይ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ከጂኦፖለቲካ አንፃር በቀጣናው የሀገሪቱን ተደማጭነት ለማሳደግ፤ የተሳለጠና ደህንነቱ የተረጋገጠ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖር፤ በከፍተኛ ፍጥነት ቁጥሩ እየጨመረ ላለው ህዝብ ዘላቂ ጥቅም ለማስከበር የባሕር በር ጨዋታ ቀያሪ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።

የባሕር በር ጥያቄ ማንሳት እንደ ነውር መታየቱ ቀርቶ የዜጎች አጀንዳ ወደ መሆን መጥቷል ያሉት አቶ ሙሉዓለም፤ ይህንን ተከትሎ ጥያቄው ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቱን ተናግረዋል።

ይህ ፍትሐዊ የባሕር በር ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኝ የተጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት መቀጠል እንዳለበት እና በተለይም የቀጣናው ሀገራት እርስበርስ ከለመተማመን አባዜ ወጥተው በሰጥቶ መቀበል መርህ እንዲሰሩ ጠንካራ ሥራ መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ጋዜጣ ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...