የቤንዚል፣ የነጭ ናፍጣ እና የኬሮሲን ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል

Date:

የነሐሴ ወር የቤንዚል፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን እና የአውሮፕላን ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል አለ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፡፡

ሚኒስቴሩ ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነሐሴ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት የቤንዚል፣ የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲንና የአውሮፕላን ነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 127 ነጥብ 22 ብር እንዲሁም ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 124 ነጥብ 55 ብር ብቻ እንዲሸጥ መወሰኑን የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወንድሙ ፍላቴ  ተናግረዋል፡፡

የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎችም በነዳጅ ውጤቶች ግብይት በአዋጁና በአሠራር መመሪያው መሠረት ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከጂሃድና ከእምቢተኝነት ውጭ ሌላ መንገድ የለም!

የኢራኑ ከፍተኛ መሪ ሞጅተባ ኻመነኢ እሁድ ዕለት በቴሌግራም ገጻቸው...

አሜሪካ እና ኢራን ዳግም ወደ ድርድር ?

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ድርድር ሙሉ በሙሉ እንዳልወጣች፣ ነገር...

እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት የሐማስ ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣን መገደሉ ተዘገበ

እስራኤል እሁድ ዕለት በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት በሐማስ የሚመራው የፍልስጤም...

አሰቃቂውን ጥቃት የፈጸሙ ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ ፓትርያርኩ ጠየቁ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት...