የብርቱካን ሚደቅሳ “መመለስ” መጽሐፍ ተመረቀ።

Date:

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በአቋም ጽናትና በአመራር ብቃቷ በምትታወቀው ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የተዘጋጀው “መመለስ፦ ቦጌ ትውስታዎቼ” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ በርካታ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል።

ብርቱካን ሚደቅሳ በዚህ መጽሐፏ ታሪኳን የተረከችበት፣ ልምዷን ያካፈለችበት፣አስገራሚውን የሕይወት ታሪኳን በመጽሐፍ መልክ እንዳዘጋጀች በመድረኩ ተገልጿል።

በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ የመጽሐፉ አርታዒያን መሠረት አበጀ፥ይኩኖአምላክ መዝገቡ ንግግር አድርገዋል።

አበበ ባልቻ እና ቆንጂት ስዩም ከመጽሐፉ የውስጥ ገፆች ለታዳሚው አንብበዋል።

በሶሊያና ሽመልስ አወያይነት መዓዛ ወርቁ፣ ሕይወት ተፈራ፣ ቴዎድሮስ አጥላውና ዳዊት ብርሃኑ ሃሳቦቻቸውን አጋርተዋል።

“መመለስ: ቦጌ ትውስታዎቼ” መጽሐፍ በ37 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን በ292 ገፆች ተቀንብቦ ለንባብ በቅቷል። በቅርቡ በተለያዩ የመጽሐፍ መደብሮች በኩል ለገበያ እንደሚቀርብም ተገልጿል።

የዚህ ፕሮግራም ብቸኛ የሚዲያ አጋር አርትስ ቴሌቪዥን ሲሆን ሙሉ የምረቃ ዝግጅቱን በቅርቡ ለተመልካቾች ያደርሳል።
Arts tv

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...