የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ቀጥሎም ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያመሩ ተገልጾ ነበር።
በወጡት ሪፖርቶች ፕረዚደንቱ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ መሐመድ ቢንዛይድ የጤና ሁኔታ ጋር ተያይዞ ተራዝሟል። ሁለቱ የሀገር መሪዎች በስልክ ውይይት ማድረጋቸውም ነው የተገለጸው።
ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉዞስ ?
የቱርክ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ፕረዚዳንቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉዞ እንደተጠበቀ ነው ሲል አስታውቋል።
ፕረዚዳንቱ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ግብዣ ወደ አዲስ አበባ እንደሚጓዙ የገለጹት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ቡርሃኔትን ዱራን ውይይቶቹ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች እንዲሁም በክልላዊ እድገቶች ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ድርድር የተጠናቀቀባቸው እንደ ንግድ፣ የመከላከያ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ላይ ስምምነቶች እና ሰነዶች እንደሚፈረሙ ይጠበቃል ሲሉም አክለዋል።
