የትግራይ ህክምና ማሕበር፣ ለጤና ባለሙያዎች የደሞዝና ጥቅማጥቅሞች ጥያቄ መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቀ።
ማሕበሩ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ለጤና ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ፣ መንግሥት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄና መብት ተገቢውን ትኩረትና ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፣ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ እየጣሰ ተገቢ ያልሆነ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታውቋል።
እነዚህ የሞያ አጋሮቻችን እንዲፈቱ አስፈላጊው ጫና እንዲደረግ ለጤና ሚኒስቴር ያሳሰበው ማሕበሩ፤ ሁሉም የሞያ ማህበራትና የጤና ባለሞያዎች ለችግሮቹ መፍትሄ ለማበጀት ግልፅና ሁሉን ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግም ጠይቋል።
በተመሳሳይ የኦሮሚያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ በመላ አገሪቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ያነሱትን የመብት ጥያቄ እንደሚደግፍ አስታውቆ፣ መንግሥት ለጥያቄያቸው ምላሽ እንዲሰጥ መጠየቁ ይታወሳል፡፡
