የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  የውጭ ምንዛሪ ገበያ  ለማሻሻል እርምጃ ወስጃለሁ  አለ

Date:

የለውጥ እርምጃዎቹ የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ ገበያ ከዓለም አቀፍ አሠራር ጋር ከማጣጣም ባሻገር ለአስመጪዎችና ለውጭ ሀገር ተጓዦች የተሻለ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ ናቸው ብሏል።

ዛሬ የተደረጉ የማሻሻያ እርምጃዎች ምንድናቸው ?

  1. ለአስመጪዎች የቅድመ ክፍያ (አድቫንስ ፐይመንት) መጠንን ከ5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወደ 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከፍ ተደርጓል።

ይህ የማሻሻያ እርምጃ አስመጪዎች ለውጭ ሀገራት አቅራቢዎቻቸው የሚያደርጉትን የውጭ ምንዛሪ ቅድመ ክፍያ (አድቫንስ ፐይመንት) መጠን የሚገድበውን የቆየ አሠራር ለመለወጥ እንደሚረዳ ተገልጿል።

በመሆኑም፤ ብሔራዊ ባንክ በአስመጪዎች ላይ የተጣለውን የቅድመ ክፍያ ገደብ ከፍ ማድረጉን አሳውቋል።

” ከአቻ ሀገራት ተሞክሮ በመነሣትና ለብዙ ዓመታት ለውጥ ሳይደረግበት የቆየውን አሠራር የመለወጥን አስፈላጊነት በመገንዘብ፣ ሸቀጦችን ከውጭ ለማስገባት ሊከፈል የሚችለውን የቅድመ ክፍያ መጠን ከ5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወደ 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከፍ ተደርጓል ” ብሏል።

  1. ለውጭ ሀገር ተጓዦች የሚፈቀደውን የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ መጠን ከፍ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ” ለውጭ ሀገር ተጓዦች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል ወደ ውጭ ሀገር ለሚጓዙ ኢትዮጵያውያን በጥሬ ገንዘብ የሚፈቀደው የውጭ ምንዛሪ መጠን እንዲጨምር ተደርጓል ” ሲል አሳውቋል።

በአዲሱ ገደብ መሠረት ለግል ተጓዦች የሚፈቀደው የውጭ ምንዛሪ ወደ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ ለንግድ ሥራ መንገደኞች ደግሞ 15 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሆኗል፡፡

ይህንንም የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ ወይም በካርድ መውሰድ ይቻላል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ያላቸው ግለሰቦች ከሂሳባቸው ላይ በካርድ መጠቀም የሚችሉት የውጭ ምንዛሪ መጠን ከ10 በመቶ ወደ 20 በመቶ ከፍ እንዲል ሆኗል፡፡

  1. የባንኮችን የውጭ ምንዛሪ ክፍያዎችን ሥርዓት ለማስያዝ እርምጃ ተወስዷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ” በኢትዮጵያ የሚሠራባቸውን ከውጭ ምንዛሪ ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ ክፍያዎችን ከዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ጋር ለማጣጣም ሲባል ባንኮች ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎት የሚያስከፍሏቸው ወጪዎች ተወዳዳሪነትን፤ ግልጸኝነትንና ምቹነትን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሆኑ አበረታታለሁ ” ብሏል።

በዚሁ መሠረት፣ ከገቢ ንግድ፣ ከአገልግሎት ክፍያ ወይም ከጥሬ ገንዘብ ጋር በተያያዘ ባንኮች ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎት የሚያስከፍሏቸው ማናቸውም አስተዳደራዊ ወጪዎችና ክፍያዎች ከግንቦት 18፣ 2017 ጀምሮ ከ4 በመቶ እንዳይበልጡ ተወስኗል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ ከውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ ወጪዎች ለተጠቃሚዎች ግልጽና ቀላል መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ባንኮች የሚያስከፍሏቸውን የተለያዩ ተጨማሪና ጥቃቅን የአገልግሎት ወጪዎች እንዲያስቀሩ ባንኩ መመሪያ አስተላልፏል፡፡

በመጨረሻም፣ ከውጭ ምንዛሪ ግብይት ጋር የተያያዙ የባንኮችን አስተዳደራዊ ክፍያዎች ግልጽነት ለማረጋገጥ ብሔራዊ ባንክ ከሰኔ ወር 2017 ጀምሮ በድረ ገጹ ላይ መረጃዎቹን በመደበኛነት ለሕዝቡ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...

ትራምፕ “በኢራን ላይ ሊፈጸም ታቅዶ የነበረውን ጥቃት አንፈጽምም” አሉ

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ አጋር ሀገራት መሪዎች...

በነዳጅ ጭማሪ በኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በጸጥታ...

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 9 ወራት 83,000 ህፃናት ተወልደዋል

ከሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ዘግይተው...