የትግራይ የጤና ባለሙያዎች የ17 ወራት ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው በሰልፍ ጠየቁ

Date:

የትግራይ የጤና ባለሙያዎች የ17 ወራት ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው በሰልፍ ጠየቁ

የትግራይ ክልል የጤና ባለሙያዎች በክልሉ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ሳያገኙ የቀሩት የ17 ወራት ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው በሰልፍ ጠየቁ። የጤና ባለሙያዎቹ ምቹ የስራ ሁኔታ እንዲፈጠርላቸውም ጥያቄ አቅርበዋል።
 
ባለሙያዎቹ ጥያቄያቸውን ያሰሙት፤ ትላንት ረቡዕ ሚያዝያ 29፤ 2017 ዓ.ም. በመቐለ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ የጤና ተቋማት ውስጥ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ነው። ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የጤና ተቋማት እንደሚካሄድ የተገለጸውን ይህ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው የትግራይ የጤና ባለሙያዎች ማህበር ነው። 

የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍስሃ አሸብር የጤና ባለሙያዎች በትግራይ ጦርነት ወቅት በስራ ገበታቸው በመገኘት ለህዝብ አገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል። የጤና ባለሙያዎቹ የህክምና አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩት፤ ለ17 ወራት ያህል ደመወዝ ሳይከፈላቸው እንደነበርም ጠቁመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...