የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮምሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) የቻይና ሕዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባኤ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበር እና የቻይና የኢንዱስትሪና የንግድ ፌዴሬሽን ሊቀመንበር ጋኦ ዩንሎንግ እና የልዑክ ቡድናቸውን ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ከ3 ሺህ 500 በላይ ቻይናውያን 9.5 ቢሊየን ዶላር ፈሰስ አድርገዋል ፡፡
በመጪው ግንቦት 4 እና 5/2017 በሚደረገው የኢንቨስት ኢን ኢትዮጵያ ፎረም ላይ ቻይናውያን እንዲሳተፉ ኮሚሽነር ዘለቀም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
መረጃው እንደሚያሳየው ጋኦ ዩንሎንግ በቻይና በተለያየ ደረጃ ያሉ ከ55ሺ በላይ የንግድ ማህበራት በኢትዮጵያ መጥተው መዋለንዋያቸውን እንዲያፈሱ እንደሚደግፉ ገልጸዋል፡፡
