የኢትዮጵያ ኢነርጂ ሽግግር

Date:

ኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት እና የኢኮኖሚ ተግዳሮቶቿን ለመቅረፍ የኒውክሌር ኢነርጂን ለሰላማዊ ልማት ለመጠቀም ቁርጠኛ አቋም መያዟን አስታወቀች።

በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው ሁለተኛው የኒውክሌር ኢነርጂ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ፤ ሀገሪቱ ከአቶሚክ ኢነርጂ የምትፈልገው “ኪሎዋት እንጂ የጥይት አረር አይደለም” በማለት የሰላማዊ አጠቃቀም ፍላጎቷን በግልጽ አስምረውበታል።

ኢትዮጵያ እስካሁን በታዳሽ ኃይል ላይ ብትመሰረትም፣ የነባር የኃይል ምንጮች አቅርቦት ከፍላጎቱ ጋር ሊመጣጠን አለመቻሉ ለዚህ ሉዓላዊ ውሳኔ መነሻ ሆኗል።

ሀገሪቱ ከሩሲያው ሮሳቶም ጋር የጀመረችው ስምምነትና በዓለም አቀፉ የኒውክሌር ኤጀንሲ መሪነት የሚከናወነው ኃላፊነት የተሞላበት አስተዳደር፣ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለህዝቦቿ ብልጽግና ለማዋል የያዘችውን ስልታዊ እቅድ የሚያጠናክር ነው።

ይህ እርምጃ ኢትዮጵያን በኃይል አቅርቦት ራሷን የቻለችና በቴክኖሎጂ የላቀች ሀገር ለማድረግ በሚደረገው ጉዞ ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...