የአርቲስት ሰሎሞን ተካልኝ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ

Date:


ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በድንገተኛ ህመም በ57ኛ ዓመቱ ህይወቱ ያለፈው፣አርቲስትና አክቲቪስት ሰሎሞን ትናንት አትላንታ ውስጥ፣ “ኢተርናል ሒልስ ሜሞሪያል ጋርደን፣በተባለ የመቃብር ሥፍራ ላይ የቀብር ሥነ-ስርዓቱ ተፈጽሟል።


ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ ቀደም ብሎ፣በአትላንታ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣የጸሎተ ፍትሓት መርሐ ግብር መካሄዱንም፣ባልደረባችን ታሪኩ ኃይሉ ዘግቧል።


ሰሎሞን ተካልኝ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ካለው ኮረብታማ ሰፈር ከወላጆቹ ከአቶ ተካልኝ መሃሪና ከእናቱ ከወይዘሮ ታዱሽ ተሰማ አብራክ እንደ ጎርጎሮሳዊው ጊዜ አቆጣጠር ጥቅምት ሰባት ቀን 1968 መወለዱን በሕይወት ታሪክ ማኀደሩ ላይ ተመልክቷል።


ሰሎሞን የሙዚቃ መሳሪያዎች ቅንብርና ውህደት የሚወድ የነበረ ቢሆንም፣የእርሱ ታላቁ መሳሪያ የነበረው ግን፣የራሱ የታደለው የፈጥሮው ድምጽ እንደነበረ ተወስቷል።


በየጎዳናው በከበሮ ታጅቦ ከመዝፈን ጀምሮ፣በደተሟላ የምሽት ክለብ እስካደገበት ድረስ ለታዳሚዎቹ ደስታና ስሜት ሲያጋራ መቆየቱም ተገልጿል።


በኋላም በአክቲቪስትነት፣ በሬዲዮና በሌሎች የተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያ አውታሮች፣የፖለቲካ አቋሞቹን ሲያራምድ ቆይቷል።
ሰለሞን በሚያስተላልፋቸው ፖለቲካዊ ሃሳቦቹ ከአንድ ወገን ብርቱ ነቀፋ እና ትችት ሲያስተናግድ ከሌላ ወገን ደግሞ ድጋፍ ሲቸረው ቆይቷል።
ቤተሰቦቹ፣ጓደኞቹና ወዳጆቹ በተገኙበት ግብዓተ መሬቱ የተፈጸመው ሰሎሞን ተካልኝ፣የአራት ልጆች አባት ነበር።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...