የዘንድሮው የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከአምናው የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን ወስነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በከተማ አስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በየዓመቱ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።
የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰአት በኋላ ይፋ ይሆናል ተብሏል።
በቀጣይ ጥቂት ቀናትም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤት ይፋ ይደረጋል ነው የተባለው።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 ዓ.ም 70 ሺህ 525 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደዋል።
