የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር 275 ሚሊዮን ብር ከቅጣት ሰበሰበ

Date:

ደንብ አስከባሪ መስሪያ ቤቱ ‘’ግንዛቤ ሳይሰጥ ቅጣት ላይ በርትቷል’’ በሚል ቢተችም ‘’እኔ ግን አልቀበለውም’’ ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራውን ባልሰራ ተቋማትና ግለሰቦች የሚከፍሉት የቅጣት መጠን ከአሁኑ በእጥፍ ይሆን ነበር ብሏል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከወንዝ ዳር ልማትና ከፈሳሽ አወጋገድ ጋር ተያይዞ የጥፋቱ የቅጣት መጠን ወስኖ መቅጣት መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

ይህንን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ግንዛቤ ሳይኖረንና አስቀድሞ ሳይነገረን ወደ ቅጣት መገባቱ ተገቢ አይደለም በማለት ይናገራሉ፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበኩሉ አሁን ላይ ገቢው ከፍ ያለ ቢመስልም የደንብ ጥሰቶቹን ባልከላከል ከዚህ ይበልጥ ነበር ሲል መልሷል፡፡

ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ያሁኑ ቅጣት የተጋነነ መስሎ ይታያል ሲሉ የነገሩን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ናቸው፡፡

ተቋሙ የተሰጠው ስልጣን ደንብ ማስከበር ነው ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ናቸው፡፡

እየተቀጣ ያለው ጥፋተኛ ነው ብለዋል፡፡ ተቋሙ ከግንዛቤ ይልቅ ቅጣት ላይ ትኩረቱን አድርጎል ተብሎ የሚሰጠውን አስተያየት ሃላፊው አይቀበሉትም፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/fbhgftr/

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...