የአፍሪካ ልማት ባንክ ለዳሸን ባንክ የ40 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ዋስትና ብድር አፀደቀ

Date:

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለዳሸን ባንክ የ40 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ዋስትና ብድር እንዳፀደቀ ዛሬ ሚያዝያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በዳሸን ባንክ ዋና መሳሪያ ቤት በተከናወነ ሥነሥርዓት ይፋ ተደርጓል።

አህጉራዊው የልማት ባንክ ያደረገው የዋስትና ብድር የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍን ለማጠናከር፣ አነስተኛ፣ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን እና የሀገር ውስጥ ኮርፖሬሽኖችን ለመደገፍ ያለመ ነው ተብሏል።

የተፈቀደው የፋይናንስ ዋስትና ብድር የኢትዮጵያን የግብርና እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎችን ለማነቃቃት ወሳኝ የሆኑትን እንደ ማዳበሪያ፣ ፋርማሲዩቲካል፣ የፀሐይኃይል ፓነሎች እና የእርሻ ማሽነሪዎችን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ድጋፍ ያደርጋልም ተብሏል።

ዳሸን ባንክ ያገኘው ድጋፍ የገቢ እና የወጪ ንግድ ፋይናንስ መስፈርቶችን እንዲያሳልጥ በማድረግ ባንኩ የኢትዮጵያ ወሳኝ የኢኮኖሚ ዘርፎች ለመደገፍ ያለውን አቅም የሚያሳድግ እንደሆነም ተነግሯል።

በዚህ የንግድ ፋይናንስ ዋስትና ብድር መሰረት የአፍሪካ ልማት ባንክ በዳሸን ባንክ ለሚቀርቡ ክፍያ ላልተከፈለባቸው ከንግድና ፋይናንስ ጋር ለተገናኙ ሰነዶች የባንክ ፍቃድ ዋስትና እንደሚሰጥም ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...