በዓለም ለ136ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን የላብ አደሮች ቀን በኢትዮጵያ በተለያዩ ሁነቶች በመከበር ላይ ይገኛል።
የመንግስትና የግል ሠራተኞች መብት አለመጠበቅ፣ የኑሮ ውድነትና የሚያገኙት ደሞዝ አለመጣጣም፣ ከጊዜ ወደጊዜ ግጭቶች መከሰት ሌሎች ችግሮች እንዲቀረፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ቀኑ በዓለም ዙሪያ እየታሰበ መሆኑን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።
በየዓመቱ እ.ኤ.አ ግንቦት 1 ቀን የሚከበረው የላብ አደሮች ቀን (ሜይ ዴይ) የሰራተኞችን መብት ማስከበር ዋነኛ አላማው ነው።
