“የአፍሪካ ትምህርት ከቅኝ አገዛዝ ነፃ መውጣት አለበት”

Date:

በቅኝ ግዛት ተጽዕኖ ሥር ያለው የአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ከሀገር በቀል ዕውቀት ይልቅ ለምዕራባውያን ሞዴሎች ቅድሚያ ስለሚሰጥ ማኅበረሰቦች ችግሮቻቸውን በራሳቸው መንገድ እንዳይፈቱ አድርጓቸዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት እና አካታች ትምህርት ክፍል ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አለማየሁ ተክለማርያም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

📜 አክለውም ቋንቋ ለመረዳት እና ችግር ለመፍታት ቁልፍ በመሆኑ ህፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር አለባቸው ብለዋል። እውነተኛ እውቀት የሚገኘው ከሀገር በቀል አስተሳሰብ እና ማኅበረሰብ ላይ በተመሠረተ ምርምር እንደሆነ የገለፁት ፕሮፌሰሩ፤ ይህም ወደ አካባቢያዊ ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ሊያመራ እንደሚችል አስረድተዋል።

“ኢትዮጵያ በወታደራዊ ኃይል በጭራሽ ቅኝ አልተገዛችም፤ ነገር ግን ባህላችን ቅኝ ተገዝቷል። ስለዚህ አስተሳሰባችንን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ማውጣት አለብን” ሲሉ ፕሮፌሰር ተክለማርያም ተናግረዋል።

📖 ፕሮፌሰሩ በቲክቶክ፣ ዩቲዩብ እና የውጭ ሚዲያዎች የተተኩት የአፍሪካ ባሕሎች እና የቃል ወጎች መነቃቃት እንደሚያስፈልጋቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...