የኢራን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መገደላቸው ተረጋገጠ

Date:


አሜሪካ እና እስራኤል ትናንት በሰነዘሩት መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ከኢራን ከፍተኛ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ በተጨማሪ ከፍተኛ የሀገሪቱ የጦር መኮንኖች መገደላቸውን የኢራን ይፋዊ የዜና ወኪል ኢርና ዘግቧል።

የኢራን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሜጀር ጄኔራል አብዱል ረሂም ሙሳቪ፣ የኢራን መከላከያ ሚኒስትር አዚዝ ናሲርዛዴህ፣ የኻሚኒ ከፍተኛ የደህንነት አማካሪ አሊ ሻምኻኒ እና የኢስላሚክ አብዮታዊ ዘበኛ (IRGC) የምድር ኃይል አዛዥ መሀመድ ፓክፑር መሞታቸው ነው የተገለጸው።

ከእነዚህ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ከፍተኛ የጦር አዛዦች የተገደሉ ሲሆን ስማቸው በሂደት ይፋ እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

ይህ ጥቃት የኢራንን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መዋቅር ክፉኛ ያናጋ ሲሆን ሀገሪቱን ያለ መሪ እና ያለ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች አስቀርቷታል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህንን ሁኔታ ተከትሎ የኢራን ሕዝብ አገሩን እንዲረከብ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን  ኢራን የአጸፋ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ ግን “ታይቶ የማይታወቅ” ምላሽ እንደሚሰጡ በድጋሚ ዝተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ንባብ ለህይወት!” ታላቅ የንባብ ሳምንት እና የመጻሕፍት አውደ ርዕይ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የንባብ ለህይወት...

በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ

በኢትዮጵያ ከ10 ሚልዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ እና ከ2...

የቶዮታ ኮሮላ መኪና በኤሌክትሪክ ሊመጣ ነዉ

የዓለማችን ግዙፍ የመኪና አምራች የሆነው ቶዮታ፤ እንደ ቴስላ እና...

ኢራንን ለመምታት የዩናይትድ ስቴትስ ጄቶች ከምድሯ ይነሱ እንደነበር እሥራኤል ይፋ አደረገች

የእሥራኤል መከላከያ ሚንሥትር እሥራኤል ካትስ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ጄቶች...