የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሁለተኛዉ ሩብ ዓመት የውጭ ምንዛሪ ጨረታ መርሐ ግብር መሰረት መደበኛ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ማክሰኞ፣ ህዳር 23፣ 2025 እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
ባንኩ በ11ኛው ዙር ጨረታ የዋጋና የውጭ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማስፈን በሚያደርገው ጥረት አካል ነዉ ያለዉን 50 ሚሊዮን ዶላር ለሽያጭ አቅርቧል።
ይህ የጨረታ መጠን በዘጠነኛዉ እና አስረኛዉ ዙር በየዕለቱ ቀርቦ ከነበረዉ 150 ሚሊዮን ዶላር አኳያ ዝቅተኛ መሆኑ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ በፊት ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ፣ ለሶስተኛው ሩብ ዓመት የውጭ ምንዛሪ ጨረታ 420 ሚሊዮን ዶላር መመደቡንና በተጨማሪም በኅዳርና ታህሳስ ወር ለሚያካሂደው ጨረታ 100 ሚሊዮን ዶላር በመደመር፣ በአጠቃላይ 520 ሚሊዮን ዶላር ለመመደብ ማቀዱን አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል።
