የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የድህረ ክፍያ

Date:

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው የፍጆታ ሂሳባቸውን ማወቅ የሚችሉበትን አሰራር በሙከራ ደረጃ አስጀምሯል፡፡

የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አንዋር አብራር እንዳሉት÷ የተጀመረው አሰራር ከድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቅረፍ ያስችላል፡፡

ከደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ደንበኞቹ ባሉበት ሆነው የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም የቆጣሪ ንባባቸውን የሚያስገቡበት የቴሌግራም ቻትቦት የሙከራ ትግበራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

የሙከራ ትግበራው ከ16 ሺህ በላይ የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ባሉበት የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ቁጥር አራት የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ላይ ብቻ ተጀምሯል ነው ያሉት፡፡

በዚህም ከየካቲት 13 ቀን እስከ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ደንበኞች የፍጆታ ንባባቸውን በቀላሉ በቤታቸው ሆነው በ @eeuchatbot ለተቋሙ እንዲልኩ ጥሪ መቅረቡን ጠቁመዋል፡፡

የዲጂታል አሰራሩ ለደንበኞች በቀላሉ ተደራሽ ለመሆን፣ የፍጆታ ሂሳብን በወቅቱ ለመፈጸም፣ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ጊዜና ወጪን ለመቆጠብ ያስችላል ማለታቸውን ፋና ዘግቧል፡፡

በሙከራ ደረጃ የተጀመረው አሰራር ያሉበትን ክፍተቶች እና ጥንካሬዎች በመለየት በቀጣይ በሌሎች ሪጅኖች እና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለማስፋት መታቀዱንም ገልጸዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ንባብ ለህይወት!” ታላቅ የንባብ ሳምንት እና የመጻሕፍት አውደ ርዕይ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የንባብ ለህይወት...

በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ

በኢትዮጵያ ከ10 ሚልዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ እና ከ2...

የቶዮታ ኮሮላ መኪና በኤሌክትሪክ ሊመጣ ነዉ

የዓለማችን ግዙፍ የመኪና አምራች የሆነው ቶዮታ፤ እንደ ቴስላ እና...

ኢራንን ለመምታት የዩናይትድ ስቴትስ ጄቶች ከምድሯ ይነሱ እንደነበር እሥራኤል ይፋ አደረገች

የእሥራኤል መከላከያ ሚንሥትር እሥራኤል ካትስ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ጄቶች...