የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል በአላቂ እቃዎች እና መድኃኒቶች እጥረት ምክንያት መስጠት ከሚገባው አገልግሎት በሦስት እጥፍ ያነሰውን እየሰጠ መሆኑን ገለጸ

Date:

የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል በመድኃኒቶችና በአላቂ እቃዎች እጥረት ምክንያት መስጠት ከሚገባው በ3 እጥፍ ያነሰ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ህሩይ አሊ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ካላት የሕዝብ ቁጥር አንፃር ከሚያስፈልጋት የልብ ሕክምና መስጫዎች ወስጥ በሕጻናት ዘርፍ ብቸኛው ማዕከል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ነገር ግን በአቅሙ ልክ እየሰራ እንዳልሆነ ተጠቁሟል።

የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ “በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሚቀርቡ መድኃኒቶች ቢኖሩም፤ ከሚያስፈልገን አንፃር በቂ አይደለም” ብለዋል።

“በሁሉም በኩል መነሳሳቶች አሉ ነገር ግን አሁንም ችግሮቹ አልተፈቱም አቅማችንንም ሙሉ በሙሉ መጠቀም አልቻልንም” ሲሉም ተናግረዋል።

የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከሉ ከዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና ከጳውሎስ ሆስፒታል ጋር በጋራ ሥራዎች እየተሰራ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

“ነገር ግን አሁንም ወረፋ የሚጠብቁ እና በየቀኑ ለሕክምና የሚመጡ ታካሚዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው” ብለዋል አቶ ህሩይ አሊ።

ከዚህ በፊት በተደረገ ጥናት ኢትዮጵያ 24 የልብ ሕክምና መስጫዎች ቢያስፈልጓትም፤ ግማሹን እንኳን ማሟላት እንዳልተቻለ ነው የተገለጸው።

በተለይ በሕጻናት የልብ ቀዶ ሕክምና ማዕከልነት ብቸኛው የሆነው ማዕከልም 80 ከመቶ የሚሆኑትን መድኃኒቶች ከውጭ የሚያስገባ በመሆኑ እና ውድ በመሆናቸው በአቅሙ ልክ መስራት እንዳልቻለ ተመላክቷል።

በዚህም ማህበረሰቡም መከላከሉ ላይ ማተኮር አለበት የተባለ ሲሆን፤ ሕጻናት በተደጋጋሚ ቶንሲል የሚከሰትባቸው ከሆነ በቶሎ ወደ ሕክምና በመሄድ መመርመር አለባቸው ተብሏል፡፡ እንደ ትምህርት ቤት ያሉ ተቋማትም ሕብረተሰቡን ማስተማር ላይ ማተኮር እንዳለባቸው ተገልጿል።

(አሐዱ ሬድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...