“ድምፃዊ ነኝ እንጂ የግጥምና ዜማ ችሎታ የለኝም” ኩኩ ሰብስቤ

Date:

አንጋፋዋ ድምፃዊት  ኩኩ ሰብስቤ በቅርቡ ለሙዚቃ አድማጭ ባቀረበችውና የመጨረሻዬ ባለችው “ደጅአዝማች” አልበም ዙሪያ ከኤፍ ኤ አዲስ 97.1መሰንበቻ ሬድዮ ፕሮግራም ጋር ቆይታ አድርጋለች።

በሙዚቃ ሕይወት ከቆየችበት ዘመን አንፃር ሰርታ ለአድማጭ ያበቃቻቸው አልበሞች  ቁጥር አነስተኛ መሆኑን የምታነሳው ድምፃዊት  ኩኩ ሰብስቤ ከደጅ አዝማች በኋላ ከአልበም ውጪ በሌሎች መንገዶች እንደምትቀጥል ገልፃለች።

በደጅ አዝማች ስራ ውስጥ ከተካተቱት ስራዎች መካከል “ሳለኝ” የተሰኘው የሙዚቃ ስራ የግጥማና ዜማ ደራሲ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ለድምፃዊቷ እህት መታወሻነት የሰራው ሙዚቃ እንደሆነ ተናግራለች።

ከእዚህ በተጨማሪ በክራር ብቻ ታጅባ የሰራችው ብቸኛ ሙዚቃ እንደሆነ ያነሳችው ኩኩ ከእዚህ በኋላ በነጠላ ዜማ ሆነ በግማሽ አልበም ስራዎቿ ውስጥ ይህንኑ እንደምቀጥል አንስታለች።

የአልበሙ መጠሪያ የሆነው ደጅአዝማች አስቀድሞ በተሰራበት አጋጣሚ ለብቻዋ አቀንቅናው እንደነበር በቆይታዋ ያነሳችው ኩኩ ሰብስቤ በኋላ ላይ ቴዲ አፍሮ ተሳትፎ ካደረገበት በኋላ ሙዚቃው ተጨማሪ ውበት ሊያገኝ እንደቻለ ገልፃለች።

ሙዚቃው “ወደ ኋላ በትዝታ መልሶኛል” የምትለው ድምፃዊቷ “ከእነ አለማየሁ እሸቴ፣ ኤፍሬም ታምሩ እና ቴዎድሮስ ታደሰ ጋር የመስራት ያክል ጥሩ ስሜት ይሰጣል።” ስትል ተናግራለች።

ከቀደመው ዘመን እስከ አሁን ባለው ሂደት ውስጥ ከወጣትና አንጋፋ የግጥምና ዜማ ደራሲያን ጋር መስራቷ እንደሚያስደስታት በቆይታዋ ያነሳችው ድምፃዊቷ በእዚህ ዘመን ካሉ ወጣት ደራሲያን መካከል ደግሞ ናትናኤል ግርማቸው የይልማ ገ/አብን መንገድ የሚከተል ባለሙያ ነው ስትል ገልፃዋለች።

ከኤፍ ኤ አዲስ 97.1መሰንበቻ ሬድዮ ፕሮግራም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...