የኢትዮ ቴሌኮምን ሼር የገዙ ሰዎች ዕጣ ፋንታ

Date:

ከዚህ ቀደም የኢትዮ ቴሌኮምን የሼር ሽያጭና የተሸጠው ሼር ከApril 25 ቀን 2025 በኋላ እውቅና ሳያገኝ (IPO) Intial Public Offer ተንጠልጥሎ መቆየቱን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ዘገባ ማቅረቤ ይታወሳል።

በወቅቱ ከነበሩኝ ስጋቶች መካከል አንዱ በ2024 በጸደቀው Intial Public Offer 10/30 ዳይሬክቲቭ መሰረት ሼር የገዙ ሰዎች ተገቢና ሕጋዊ መብታቸው እስከ አሁን ድረስ እውቅና ባለማግኘቱ ምክንያት ከአንጻራዊ የዓመታዊ ትርፍ ድልድል (12.6 ቢሊየን ብር የትርፍ ድልድል ለመንግስት ገቢ ሁኗል) ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ነበር።

47 ሺ የሚጠጉትና የኢትዮ ቴሌኮምን ሼር የገዙ ሰዎች ገንዘባቸው እስከ አሁን ድረስ ታግቷል። ተቀባይነት ሳያገኝ ተንጠልጥሎ በመቅረቱ ምክንያት ዘንድሮ ኢትዮ ቴሌኮም ካገኘው የ12.6 ቢሊየን ብር የተጣራ ትርፍ መጋራት አልቻሉም።

ሌላው ቢቀር እንኳን ገንዘባቸውን ባንክ ቢያስቀምጡ ኑሮ ማግኘት የሚገባቸውን ዝቅተኛ ወለድ አላገኙም። እስከ አሁንም ገንዘባቸው በአክስዮን ባለቤትነት እውቅና አግኝቶ የሚመዘገበው መቼ እንደሆን አንዳችም ፍንጭ የለም። ገንዘብም በየእለቱ መጋሸቡን ቀጥሏል።

የIPO አክሲዮን ሽያጭ ከApril 25 ቀን 2025 ጀምሮ የተጠናቀቀ ቢሆንም እስከ አሁን የአክሲዮን ገዢዎች ገንዘብ በኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ድርሻ ባለቤትነት ተቀባይነት ሳያገኝ በቴሌ ካዝና ውስጥ ተንጠልጥሎ በመቅረቱ ገንዘባቸው በግሽበት እየደቀቀ ነው።

እንደዚህ ዓይነቱ በባለ ሁለት ስለት የሚገዘግዝ አሰራር በካፒታል ገበያው ላይ የሚያስከትለው እምነት የማጣት መዘዝ ቀላል ስለማይሆን አሁንም ቴሌኮም እራሱን የካፒታል ገበያ ባለስልጣንም ሕጉን ሊመረምርና በሕግ የተሰጠውን ስልጣን ሊያስከብር ይገባል።

ከሙሼ ሰሙ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...

ሕወሓት ድብረጺዮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

የክልሉ ፕሬዚዳንት ተደርገው የተመረጡት  ድብርጺዮን ገ/ ሚካዔል (ዶ/ር)  ቃለ...

” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” – ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ...

የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም

የጥንት ኢትዮጵያዊያንአርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ ሚያዚያ...