“ቃሊ” የተሰኘው የድምጻዊ እስራኤል በሻዳ አዲስ አልበም ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም በድምፃዊው የዩቱብ ቻናልና በሁሉም የዲጂታል መተግበሪያዎች ለአድማጭ እንደሚደርስ ድምፃዊው በዛሬው እለት በቢሾፍቱ ከተማ ፒራሚድ ሪዞርት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
“ቃሊ” አልበም በርካታ አንጋፋና ወጣት የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሣተፉበት ሲሆን 12 ያህል ሙዚቃዎች ተካተውበታል።
ድምጻዊ እስራኤል በሻዳ በ2023 የኦሮሞ ምርጥ አዲስ ድምጻዊ ተብሎ እንደተሸለመ የተገለፀ ሲሆን የኦሮሞ ቱባ ባህሉንና ታሪኩን እንዲሁም ጥበቡን የተካተተበት ይህ አልበም ታላቁ የሙዚቃ ሰው አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ የመጨረሻውን ማስተሪንግ እንደሰራው ተነግሯል።
“ቃሊ” አልበም የፊታችን ግንቦት 23 ሲመረቅ ኮንሰርትም እንደሚዘጋጅ የተገለፀ ሲሆን ከዚህ አልበም ምረቃ በኃላ ድምፃዊ እስራኤል በሻዳ በአዲስ አበባ ፣ በአዳማ ፣ በድሬደዋ እና በሌሎች ከተሞች የሙዚቃ ዝግጅት እንደሚያቀርብ ተገልጿል።
ድምጻዊ እስራኤል በሻዳ ከዚህ ቀደም “ናንዬ” በተሰኘው ሙዚቃው ተወዳጅነትን አትርፏል።
ድምጻዊ እስራኤል በሻዳ ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል ኢንጂነር ተመርቆ በሞያው ለአመታት እየሰራበት ይገኛል።
