የኤሌክትሮኒክስ አቤቱታ አቀራረብ እና ሙግት መመሪያ

Date:

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለጉዳዮች ፍርድ ቤት በአካል መቅረብ ሳይስፈልጋቸው፣ በተፈቀደላቸው የኤሌክትሮኒክ ስርዓቶች በመጠቀም፣ ባሉበት ሆነው በማንኛውም ጊዜ አቤቱታም ሆኑ ሌሎች ሰነዶችን ለፍርድ ቤት እንዲያቀርቡ እና በሙግት ሂደቱም እንዲሳተፉ የሚያስችላቸው የኤሌክትሮኒክ አቤቱታ አቀራረብ እና ሙግት መመሪያ አውጥቷል፡፡

በጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ነሐሴ 23/2017 ዓ/ም ተፈርሞ የጸደቀው ” የኤሌክትሮኒክ አቤቱታ አቀራረብ እና ሙግት መመሪያ ቁጥር 25/2017 ”  ከመስከረም 23 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ለሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል የተባለው መመሪያ በክልል ፍርድ ቤቶች አማካኝነት በውክልና በሚታዩ የፌዴራል ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው ፍርድ ቤቶቹ ይህን ቴክኖሎጂ ለመተግበር የሚያስችል መሠረተ ልማት ያላቸው መሆኑ ሲረጋግጥ ነው ይላል።

መመሪያው ስለ የኤሌክትሮኒክ አቤቱታ እና ሙግት አቀራረብ፣ ስለ ስርአቱ አጠቃቀም እና ደህንነት ፣ የሰነዶች አቀባበል ሁኔታ ፣በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ስለሚቀርቡ ቃለ መሃላዎች ጨምሮ ሌሎችንም ጉዳዮች በዝርዝር ይዟል።

አዲሱ ” የኤሌክትሮኒክ አቤቱታ አቀራረብ እና ሙግት መመሪያ ቁጥር 25/2017 ” ምን ምን ነጥቦች ተካተዋል

• በኤሌክትሮኒክ አቤቱታ አቀራረብ እና ሙግት ስርዓት አማካኝነት በኤሌክትሮኒክ መልክ ለፍርድ ቤት የቀረቡ ሰነዶች፣ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የተያዙ ሰነዶች፣በኤሌክትሮኒክ መልክ በፍርድ ቤት የሚከናወኑ የርቀት መስማት እና ክርክሮች በፍርድ ቤቱ በአካል በመቅረብ ከሚደረጉ መስማት እና ክርክሮች እንዲሁም በፍርድ ቤቱ በወረቀት ከተያዙ ስነዶች ጋር ተመሳሳይ የሆነ ተቀባይነት እና ውጤት ይኖራቸዋል፡፡

• የስርዓቱ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰብ ተከራካሪዎች በስርዓቱ ለመጠቀም ምዝገባ ማከናወን የማያስፈልጋቸው ሲሆን በብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) መለያ ቁጥራቸው እና ለፋይዳ ባስመዘገቡት የሞባይል ስልክ ቁጥር በሚላክላቸው የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል አማካኝነት ብቻ ወደ ስርዓቱ መግባት እና መጠቀም ይችላሉ፡፡

• ግለሰብ ተከራካሪው ጠበቃ ከሆነ ወደ ስርዓቱ ለመግባት ከፋይዳ መለያ ቁጥሩ እና የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል በተጨማሪ የጥብቅና አገልግሎት ፈቃድ ቁጥሩን ማስገባት አለበት፡፡

• ማንኛውም ተቋማዊ ተከራካሪ በስርዓቱ ለመጠቀም እንዲችል ተቋሙን እና ተቋሙን ወክለው የሚከራከር(ሩ) አንድ ወይም ከአንድ በላይ ግለሰብ ተከራካሪዎችን በሚኖሩበት ጊዜ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው ፎርም ላይ በመሙላት ለዋና ሬጅስትራር አቅርቦ ማስመዝገብ አለበት፡፡

• የርቀት መስማት የችሎት ስነ ስርዓት ወቅት  ተሳታፊዎች በአካል ችሎት መቅረብ የሚጠይቀውን ስነ ስርዓት ማክበር ይጠበቅባቸዋል።

• ተሳታፊዎች በሥነ ምግባራቸው፣ በአነጋገራቸው እና በአለባበሳቸው ለችሎት ሂደቱ ያላቸውን ክብር ማሳየት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህን ስርዓት በጣሱ ጊዜ አግባብነት ያላቸው የስነ ስርዓት ህግ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል።

• ተከራካሪዎች በኤሌክትሮኒክ አቤቱታ አቀራረብ እና ሙግት ስርዓት ተጠቅመው በማንኛውም ቀን የበዓል እና የእረፍት ጊዜያትን ጨምሮ በማንኛውም ሰዓት ሰነዶች ለፍርድ ቤት ለማቅረብ ይችላሉ።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...