የእስራኤል አምባሳደር ከስብሰባ ተገደው ወጡ

Date:

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት ቤተ እስራኤላዊው አብርሃም ንጉሴ ዛሬ አፍሪካ ኅብረት የሩዋንዳውን የዘር ጭፍጨፋ ለማሰብ ካዘጋጀው ስብሰባ ተገደው እንዲወጡ ተደርገዋል።

አምባሳደር ከስብሰባው እንዲወጡ የተገደዱት፣ እስራኤል በጋዛ ፍልስጤማዊያን ላይ የምትፈጽመውን መጠነ ሰፊ ጥቃት የሚቃወሙ በርካታ አባል አገራት አምባሳደሩ በተገኙበት ስብሰባ ላይ አንካፈልም ብለው ተቃውሞ በማሰማታቸውን እንደሆነ ተገልጧል።

የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ አምባሳደሩ ከስብሰባው ተገደው መውጣታቸውን ተከትሎ በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሃሙድ የሱፍን መውቀሱን የእስራኤል ጋዜጦች ዘግበዋል።

ሚንስቴሩ፣ ድርጊቱ የዘር ጭፍጨፋ የደረሰባቸውን የሩዋንዳ ቱትሲዎች መታሰቢያ ክብር ያልሰጠ፣ ተቀባይነት የሌለውና፣ የሩዋንዳና አይሁድ ሕዝቦችን ታሪክ ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው በማለት መተቸቱን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

እስራኤል በድርጊቱ አሳሳቢነት ዙሪያ በዲፕሎማሲያዊ መስመሮች እንደምትገልጽ ጠቁማለች ተብሏል። አብርሃም የእስራኤል አምባሳደር ሆነው የተሾሙት፣ ባለፈው ዓመት ነሃሴ ነበር። [ዋዜማ]

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...