የእስራኤል የህክምና ቡድን በኢትዮጲያ ነፃ የዓይን ህክምና ሰጠ

Date:

ዘሪቱ ትባላለች ከአምስት አመት በፊት በዓይን ሞራ ምክንያት የዓይን ብርሃኗ ተጋርዶባት ነበር።

የእስራኤል የህክምና ቡድን ባደረገላት ህክምና የአይን ብርሃኗ ተመልሶ ለመጀመሪያ ጊዜ የስድስት ወር ልጇን ማየት ችላለች።

በፕሮፌሰር ሞሪስ ሃሪስተን የተመራው የዓይን ህክምና ቡድን ( ኦፕሬሽን ኢትዮጵያ ) በደሴ ከተማ ቦሩ ሜዳ አጠቃላይ ሆስፒታል ነፃ የዓይን ህክምና ሰጥቷል።

የህክምና ቡድኑ 530 ለሚሆኑ ህፃናት እና አቅም ለሌላቸው አረጋዊያን ከቀላል እስከ ውስብስብ የዓይን ቀዶ ጥገና አከናውኗል ።

በኢትዮጵያ የእስራኤል ምክትል አምባሳደር ቶሜር ባርላቪ እንዳሉት ኦፕሬሽን ኢትዮጵያ በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ከሚያጠናክሩ በርካታ የእስራኤል ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው።

ድርጅቱ የኢትዮጵያውያንን ጤና በማሻሻል በመላ አገሪቱ እየሰራ ይገኛል።

እስራኤል ከጤናው ዘርፍ በተጨማሪ በግብርና፣ በኢኖቬሽን፣ በንግድ ትብብር፣ በባህልና በሌሎች ዘርፎች እየሰራች ትገኛለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...