የከተማ መሬት አቅርቦት 69% ቢጨምርም የጨረታ አፈጻጸም 6 በመቶ ብቻ ነዉ

Date:



በከተሞች የልማት መሬት አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ቢታይም፣ በጨረታ የቀረበው መሬት መጠን እጅግ አነስተኛ መሆኑን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።

እንደሚ ተቋሙ መረጃ ከሆነ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 17.6 ሺህ ሄክታር መሬት ለልማት የቀረበ ሲሆን ይህም ከታቀደው 14,000 ሄክታር በልጦ እንዲሁም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ69 በመቶ (7,200.14 ሄክታር) ብልጫ አሳይቷል።

ይሁን እንጂ መንግስት ከቀረበው መሬት ውስጥ 30 በመቶውን በጨረታ ለማቅረብ እቅድ ቢኖረውም፣ እስካሁን ለጨረታ የቀረበው 971 ሄክታር ብቻ ሲሆን ይህም ከጠቅላላው የቀረበ መሬት 6 በመቶውን ብቻ ይይዛል።

የ2017 በጀት ዓመት  የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረበዉ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በእነዚህ ወራት በአጠቃላይ በከተሞች ከሚገኙ 6.5 ሚሊዮን ቁራሽ መሬቶች መካከል እስካሁን ከ 1 ሚሊየን 757 ሺህ 272 (27.03%) የሚሆኑት ተመዝግበዋል ብሏል።

Source: capitalethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...