የዛሬ 50 ዓመት የተፃፈውና ዘንድሮ ለሕትመት የበቃው የጋዜጠኛና ደራሲ መዝገቡ አባተ መፅሐፍ ዛሬ ግንቦት 25 2017 ዓ.ም በድምቀት ይመረቃል።
ጋዜጠኛና ደራሲ መዝገቡ አባተ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች እየተዘዋወረ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጠይቆ የተረዳውን መዝግቦ ያዘጋጀው መፅሀፍ ከ400 በላይ ገፆች ያሉት ሲሆን የመፅሐፉም አርታዒ የታሪክ ባለሙያ ብርሀኑ ደቦጭ ነው፡፡
መፅሐፉ ዛሬበአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ሲመረቅ የደራሲው ልጆች፣ ቤተሰቦችና ወዳጆች ይታደማሉ፡፡በተጨማሪም ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ፣ የሀገር ባለውለታዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
የሁነቱ አዘጋጅ ደግሞ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን መሆኑ ሲሆን የደራሲው ቤተሰቦችና መፅሀፉ የሕትመት ብርሀን እንዲያይ አድርገዋል፡፡
በመፅሀፉ ላይ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ፣ ፕሮፌሰር ሰሎሞን ሙሉጌታ እና ጋዜጠኛ ማዕረጉ በዛብህ ፣የመፅሀፍ ግምገማ የሚያቀርቡ ሲሆን የደራሲው የመዝገቡ አባተ የሕይወት ታሪክም በልጃቸው በፀሀይ መዝገቡ አባተ እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ደራሲ እና ጋዜጠኛ መዝገቡ አባተ የዛሬ 14 ዐመት ሕይወቱ ያለፈ ጋዜጠኛ ሲሆት በአገራችን በሕትመት ሚድያዎች በማገልገል የሚታወቅ ነው፡፡ከሠራባቸው የህትመት ውጤቶች መካከልም ሰንደቅ አላማችን አንዱ ነው፡፡
