የዝናብ መጠን በከተማና በገጠር አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል ይችላል

Date:

የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢፕድ በላከው መግለጫ እንደገለፀው፣አልፎ አልፎ ከሚኖረው ተደጋጋሚ የሆነ ከባድ ዝናብ ጋር ተያይዞ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ተፋሰሶች፤ የከተማና የገጠር አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ፣ የወንዞች ከፍታ መጨመር ሊያስከትል ይችላል፡፡

የክረምት ዝናብ በብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ እየተጠናከረ እንደሚሄድ በመግለጽ፣ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚስተዋል ተመላክቷል።

በሰሜን ምስራቅ፤ መካከለኛውና ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች የአየር ሁኔታ ክስተቶች አልፎ አልፎ እንደሚጠናከሩ የገለፀው ኢንስቲትዩት ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር ጠቁሟል።

ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች በሁሉም የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎችን ይበልጥብኛል እንሚጠናከር ገልጻል፡፡ በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜንና መካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚዘወተር ተመላክቷል፡፡

እርጥበቱ ለወቅቱ የግብርና ስራ እንቅሥቃሴ በአመዛኙ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው በመግለጽም፤ ስጋቶችን ለመቀነስና የሚኖሩትን መልካም አጋጣሚዎች ለመጠቀም የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦች መተግበር ያሰፈልጋል።

በቀጣይ ቀናት በአብዛኛው ተፋሰሶች ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገፀ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖር ያመላከተው መግለጫው፣ አልፎ አልፎ ከሚኖረው ተደጋጋሚ የሆነ ከባድ ዝናብ ጋር ተያይዞ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ተፋሰሶች እንዲሁም የከተማም ሆነ የገጠር አካባቢዎች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ፣ የወንዞች ከፍታ መጨመር ሊያስከትል ይችላል ብሏል።

በመሆኑም የሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት ሊኖር የሚችለው አደጋ ለመቀነስም ሆነ መልካም ዕድሎችን ለመጠቀም የተፋሰስ ተኮር የውሃ ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦች ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡

ጋዜጣ_ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...