የየካቲት 12 ሰማዕታት ፍትሕ እንዲያገኙ የሚደረግ ዓለም አቀፍ ዘመቻ

Date:

ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ የኢትዮጵያ ጉዳይ ማኅበር በቫቲካን ድጋፍ ተፈጸመው ኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመ የጦር ወንጀል፣ የሰው እልቂት እና የንብረት ውድመት በተጨማሪ ከኢጣሊያ የተደረገ ለውጦ ከግም ጉዳይን ለፍትሕ የተባለ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ያካሄዳል። ዘመቻው ሰማዕታትን በተለይ በተደራሽ ትምህርት የማቅረብ የተለያዩ ትእዛዞችን ያካሄዳል።

”ለዚህ ሁሉ ወንጀል፣ ኢትዮጵያ ያገኘችው ተገቢ የሆነ ካሳ የለም። ዋናው ነገር ፍትሕ እንዲገኝ፣ ያ ሁሉ ጭፍጨፋ፣ያ ሁሉ ወንጀል ተከናውኖ ዝም ብሎ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለት ተገቢ አለመሆኑን በማስረዳት በልዩ ልዩ መንገድ ጥረት ተደርጓል።”

የካቲት 12፤ የኢትዮጵያ ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን
መንበሩን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ፣ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ የኢትዮጵያ ጉዳይ የተባለው ማኅበር፣ በቫቲካን ድጋፍ የመርዝ ጋዝ ጭምር በመጠቀም፣ ኢትዮጵያ ላይ ተፈጸሟል ላለው  የጦር ወንጀል፣ የሰው እልቂት እና ከፍተኛ የንብረት ውድመት ተገቢውን ፍትሕና ካሳ እንዲገኝ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ያካሄዳል።

የማኅበሩ አጀማመር 

ዶቼ ቨለ ያነጋገራቸው አቶ ኪዳኔ አለማየሁ፡ ይህንን ማኅበር ከዐሥር ዓመታት በፊት በማቋቋም፣ መንቀሳቀስ መጀመራቸውን ገልጸዋል። ”እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ማተኮር የጀመርኹት፣ ከዐሥር ዓመታት በላይ፣አሁን ዕድሜዬም 90 ስለሞላ፣ለእነርሱ አስረክቤያለሁኝ፤ብዙ ኃብት ተዘርፏል፣ከእነዛ ውስጥ በቫቲካን ቤተመዝገብ ከ 500 በላይ የኢትዮጵያ ቅርሶች ቁጭ ብለው ይገኛሉ።”


ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ከ 1928  እሰከ 1934 ዓ.ም ድረስ፣አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያንውያን ከመጨፍጨፋቸው በላይ፣ሁለት ሺህ ቤተክርስቲያኖች እና 525 ቪህ ቤቶች መውደማቸው ይነገራል። እንዲሁም፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እንስሳት አልቀዋል።

የማኅበሩ ዓለም አቀፍ ጥረት

”ለዚህ ሁሉ ወንጀል፣ ኢትዮጵያ ያገኘችው ተገቢ የሆነ ካሳ የለም። ዋናው ነገር ፍትሕ እንዲገኝ፣ ያ ሁሉ ጭፍጨፋ፣ያ ሁሉ ወንጀል ተከናውኖ ዝም ብሎኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለት ተገቢ አለመሆኑን በማስረዳት በልዩ ልዩ መንገድ ጥረት ተደርጓል።”

ይኸው ማኅበር፣ ፍትህ እንዲገኝ በሚያከናውነው አለም ዓቀፍ ዘመቻ፣ ኢጣሊያ ተገቢውን ካሳ ለኢትዮጵያን እንድትከፍል፣ቫቲካን የኢትዩጵያን  ህዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፣ ኢጣልያና ቫቲካን ከኢትዮጵያ ዘርፈዋቸዋል የተባሉ ንብረቶች እንዲመለሱ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም፣የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ጣልያኖች በኢትዮጵያ ላይ ፈጽመውታል የተባለን ወንጀል እንዲመዘግብ እና፣አፊሌ በምትሰኝ የጣሊያን ከተማ ለግራዚያን የተቋቋመው መታሰቢያ እንዲወገድ እየጣረ መሆኑንም ተገልጿል።

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አቻምየለህ ደበላ በበኩላቸው ለዶቼ ቨለ እንደተናገሩት፣ የየካቲት 12 ሰማዕታትን ለአንድ ቀን አስቦ ከመዋል ባለፈ፣ በስማቸው ለትውልድ የሚተርፍ ሥራ መስራት ይገባል።

”እነሱ ተሰውተዋል እኛስ ምንድን ይዘን ነው? ይሄን ታሪክ ጥሩ ቦታ ለማድረስ የምንችለው የሚለውን መልስ ለመስጠት፣ የሚያስችለው የሚለውን መልስ ለመስጠት የሚያስችል፣ትምህርት ሊሆነን የሚችሉ የተለያዩ ዐይነት ፕሮግራሞችን እንድንሰራ ነው።”

”በትምህርት ደረጃ፣ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ኮሌጅ ድረስ ባለው የተለያዩ ሥርዓተ ትምህርት /ካሪኩለም/ ተንድፎ፣ ከሚማሩት የታሪክ ትምህርት አንደኛው እንዲሆን ለማድረግ፣ በተቻለ መጠን እንደነአብርሆት ያሉ ቤተ መጻሕፍት፣ይህ ዕለት በሚከበርበት እና ለአንድ ወር ያህል ጊዜ ተስጥቶ የበዓሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ ዓለም አቀፍ ኅብረት ለፍትኅ የኢትዮጵያ ጉዳይ ጥሪ አቅርቧል።

የሥርዓተ ትምህርት አስፈላጊነት

ከነዚህ ስራዎች መኻከል፣ የየካቲት 12 ታሪክን በስርዓተ ትምህርት ዉስጥ ተካትቶ፣ ትውልዱ እንዲማርበት ማድረግ እንደሚገባ ፕሬዚዳንቱ አስገንዝበዋል።

”በትምህርት ደረጃ፣ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ኮሌጅ ድረስ ባለው የተለያዩ ሥርዓተ ትምህርት /ካሪኩለም/ ተንድፎ፣ ከሚማሩት የታሪክ ትምህርት አንደኛው እንዲሆን ለማድረግ፣ በተቻለ መጠን አብረህሁት ያሉት በሚከበርበት እና ጊዜ የተሰጡ የባህሉ ተሳታፊ የሆነው በተቻለ መጠን እንደነ አብርሆት ያሉ ቤተ መጻሕፍት፣ይህ ዕለት በሚከበርበት እና ለአንድ ወር ያህል ጊዜ ተስጥቶ የበዓሉ ተሳታፊ ሆነው፣በዚህ ዙሪያ የተጻፉ ጽሑፎችን የማሰስ፣ ለህዝብ የማቅረብ ወጣቶች እንዲያነቡ የማድረግ፣ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት፣ በፖስተሮች፣ በተለያዩ በሲኒማ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ፣ ትውልድን ሊያስተምር የሚችል ሁኔታን ማዘጋጀት፣ በተለይም በየድርጅቱ ትምህርታዊ የሆነ ውይይት እንዲካሄድ ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት ነው።”

በየካቲት 12 ኢትዮጵያውያን በጅምላ ሰማዕታት የሆኑት፣ጣሊያን በአድዋ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ  እና ኢትዮጵያን ለመውረር ባደረገው ወረራ የተበሳጩ፣ ኢትዮጵያውያኑ አርበኞች አብርሃ ደቦጮ እና ሞገስ አስገዶም፣በኢትዮጵያዊው የፋሽስት አስተዳደር ተወካይ ኃላፊ የነበረውን ማርሻል ሩዶልፍ ግራዚያኒን ለመግደል ሙከራ በማድረጋቸው ነበር።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...